አማራ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Amhara Bank S.C (አማራ ባንክ አ.ማ)
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
የሐራጅ ማስታወቂያ ቁጥር አማራ ባንክ/52/2019
አማራ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
| ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም | የንብረት አስያዥ ስም | አበዳሪው ቅርንጫፍ | የንብረቱ አድራሻ ከተማ | ክ/ከተማ | ወረዳ | ቀበሌ | የቦታው ስፋት | የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር | የንብረቱ ዓይነት/ የሚሰጠው አገልግሎት | የጨረታ መነሻ ዋጋ /ብር/ | ጨረታው የሚከናወንበት ቀን | ሰዓት | ቦታ |
| 1 | አቶ አላዩ ጋሹ አይናለም | አቶ መንግስቱ መኩሪያ ጌታሁን | ባህር ዳር | ባህር ዳር | አፄ ቴዎድሮስ | - | 11 | 250 ካሬ ሜትር | 25568/2001 | ለመኖሪያ | 11,794,371.11 | ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም | ከ4:00 እስከ 5:00 ሰዓት | አማራ ባንክ አ.ማ ባህር ዳር ዲስትሪክት ቢሮ |
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ ወይም ሃያ አምስት በመቶ (25%) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (C.P.O) ብቻ በአማራ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት፣ በማስያዝ እና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በጽሁፍ ሲደርሰው ብቻ ነው፡፡
- የጨረታ አሸናፊው አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ሲፒኦ አይመለስለትም፤ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሃራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡ ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ በእለቱ ይመለስላቸዋል፡፡
- የሐራጅ አሸናፊ /ገዥ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን የሊዝን ክፍያን ጨምሮ፣ ግብር፣ በዋጋው ላይ ሚታሰብ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) ካለ ከስም ማዘዋወሪያ ጋር የተገናኙ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስ እና ግብሮች ገዥው/አሸናፊው/ ይከፍላል፡፡
- ተጫራቾች በሃራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ (የቀበሌ፣የመንጃ ፍቃድ፣ፓስፖርት ወይም ብሄራዊ መታወቂያ) መያዝ ይገባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የህግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ህጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የምና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሃራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ግለሰብ ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የጸደቀ መመስረቻ ጽሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ ቃለጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
- ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
- ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም ከወርካውትና ሪከቨሪ ክፍል ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ ጨረታው ከመካሄዱ ከ5 ቀን በፊት መጎብኘት ይችላል፡፡
- ጨረታው በሰንጠረዥ ላይ በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል፡፡ ነገር ግን ተበዳሪውም ሆነ መያዣ ሰጪዉ ባይገኙ ጨረታው በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
- ንብረቱን/ቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም፡፡ ገዥው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚወጣ ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡
- በባንኩ የብድር ፖሊሲ፣ መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ ፤
እስከ 100% ድረስ ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
በንብረቱ ላይ የምርት ተግባር ለሚያከናውኑ ገዥዎች ባንኩ ተጨማሪ ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
በተጨማሪም ለባንኩ የተሻለ ጥቅም የሚያስገኙከሆነ ባንኩ ለመደራደር ዝግጁ ነው፡፡ - የተጫራቾች ምዝገባ ከሃራጅ መዝጊያ ሰአት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡
- ለበለጠ ማብራሪያ አማራ ባንክ አ.ማ 0115 58 27 64 ወይም 0115-58 41 89 በስራ ሰአት ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በወንድ አንቀጽ የተጠቀሰው ሴትን እና ህጋዊ ሰውነት ላላቸው ድርጅቶችም ያገለግላል፡፡
አማራ ባንክ አ.ማህበር
✨ messages.ai_summary
Amhara Bank is selling a residential property in Bahir Dar, Azezo Tewodros, measuring 2500 sq.m, via a second-round public auction. Bidders must register with a bank-certified payment document (CPO) covering 25% of the starting price, and present valid ID or legal entity documents.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
