Purchase of Brand New Fully Electric Vehicle (Re-advertised, Urgent) EVA/NCB/EV/04/2026 - Ethiopian Veterinary Association (EVA)
Ethiopian Veterinary Association-EVA (የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማኅበር)
የኤሌክትሪክ መኪና ለመግዛት በድጋሚ የወጣ አስቸኳይ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር፡ EVA/NCB/EV/04/2026
የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማኅበር (Ethiopian Veterinary Association-EVA) ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠራ አዲስ ተሽከርካሪ (Brand New Fully Electric Vehicle) ከሀገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በአስቸኳይ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በዘርፉ የተሠማሩ፣ ብቃት ያላቸውና ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መሥፈርቶችን የሚያሟሉ አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ማኅበሩ ይጋብዛል።
- መቅረብ የሚገባቸው ሕጋዊ ማስረጃዎች (Eligibility Criteria)፤
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፊኬት፣
- በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) መመዝገባቸው የሚያሳይ ሰርተፊኬት፣
- የ2018 ዓ.ም ግብር የተከፈለበት ማስረጃ፣
- ለ2019 የግብር ዘመን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ አሊያም በጨረታ ለመወዳደር እንደሚችሉ ከገቢዎች ሚኒስቴር የተሰጠ የግብር ክሊራንስ (Tax Clearance) መረጃ፣
- በግዥና ንብረት ባለሥልጣን የአቅራቢዎች ዝርዝር (Federal Procurement Public Agency Web) ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ወይም ሰርተፊኬት፣
- የጨረታ ሰነድ አወሳሰድ፤
- ፍላጎት ያላቸውና መስፈርቱን የሚያሟሉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 (አሥራ ስድስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ በማኅበሩ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 303/306 ዘወትር በሥራ ሰዓት በአካል ቀርበው የጨረታ ሰነዱን በነጻ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ፣ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። ጨረታውን ያላሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና፤አሸናፊ ድርጅት እንደተለየ ወዲያኑ ይመለስላቸዋል።
- ተጫራቾች የቴክኒክ ሰነድ ኦሪጂናል እና የፋይናንሻል ሰነድ ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ መ/ቤታችን ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን በ11፡30 ላይ ይዘጋል። በ17ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ሆኖም የተጫራቾች ወይም የወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም።
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡-
- በስልክ ቁጥር፡- +251-115-525-020; 091189490209; 0904327608; 0911185503
- አድራሻ፡- ከእንግሊዝ ኤምባሲ (British Embassy) ወደ School of Tomorrow በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ገባ ብሎ ይመናሹ ሕንጻ ፊት ለፊት ያገኙናል።
የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማህበር
✨ messages.ai_summary
The Ethiopian Veterinary Association seeks to buy a brand new fully electric vehicle through an urgent re-advertised open tender from the domestic market. Eligible suppliers must provide TIN, VAT registration, tax payment proof, renewed business license or tax clearance, and proof of registration with the Federal Procurement Agency.
