የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ እና ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሎቶች መሰረት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የቤ/ጉ/ክ/መ/ ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ እና ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ እና ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሎቶች መሰረት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1.የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት2. ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት3. የጽዳት ዕቃዎች እና ሎት4. ደንብ ልብስ
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው
- በአቅራቢነት የተመዘገበ እና የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል ከተራ ቁጥር 1-2 ላይ የተጠቀሱትን ኦርጅናል ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11:30 ድረስ ከግ/ን/አስ/ ዳይሬክቶሬት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 ብር በጥሬ ገንዘብ በመክፈል የሚፈለገውን የእቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ(እስፔስፊኬሽን) የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚችሉ ሲሆን ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የሚያቀርቡት ዋጋ ከነቫት ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሎቶቹ ለየብቻ በመለየት የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡ የሚያስዙት የጨረታ ማስከበሪያ በቢድቦንድ ከሆነ ከ60 ቀን ያነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድቦንድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀናት ጀምሮ ካሉት 5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የዋጋውን የውል ማስከበሪያ በየሎቱ 10% በማስያዝ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በየሎቱ በተለያዩ ፖስታ በማሸግ የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ እና ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16 ኛው ቀን 4:00 ሰአት ድረስ በማስገባት ሳጥኑ የሚታሸግ ሲሆን በዚያ ቀን 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በመከፈቻው ዕለት የማይገኙ ከሆነ በሌሉበት ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን እና ሰአት የሚከፈት ሆኗል፡፡
- ሁሉም የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማ መኖሩ የሚገባው ሲሆን ስርዝ ድልዝ ሲያጋጥም በፊርማ ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱም ካሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ካሸነፈው እቃ ወይም ገንዘብ መጠን ላይ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ክልሉ ላወጣቸው የግዥ አፈጻጸም መመሪያዎች ተገዥ መሆን ሲኖርባቸው ማሸነፉ ከተነገረ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራስን ማግለል አይቻልም፡፡
- አሸናፊ ድርጅት ንብረቱን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ እና ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ድረስ ማቅረብ ግዴታ ይሆናል፡፡
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ኦርጅናል እቃዎችን የማቅረብ ግዴታ ያለበት ሲሆን እቃዎችን የምንቀበለው በሚመለከተው ባለሙያ ሲረጋገጥ ነው፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ እና ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 057775 29 39 /0913248379 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
ማሳሰቢያ፡- በማንኛውም ሁኔታ የተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ በሚከፈትበት ሰዓት የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ እና ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ
✨ messages.ai_summary
Benishangul Gumuz Regional State Urban & Infrastructure and Trade & Market Development Bureaus seek suppliers for office-use goods in four lots: stationery, electronics, cleaning materials, and uniforms. Bidders must have a valid trade license, TIN, supplier registration, and VAT registration.
