ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለድርጅታችን የሚያስፈልጉ የተለያዩ የፅዳት ማሽነሪዎች፣ የፅዳት ማሽነሪዎች መለዋወጫ አቅርቦትና የጥገና አገልግሎት፣ የመኪና ግዥ እና ኢቪ ቻርጀሮች ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
Commercial Nominees Plc (ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ)
የጨረታ ማስታወቂያ
CN/NCB/08/19
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለድርጅታችን የሚያስፈልጉ ሎት1፡- የተለያዩ የፅዳት ማሽነሪዎች (Different Cleaning Machineries)፡- Floor Scrubbing machine, backpack vacuum cleaner, Driving type electrical Road sweepers, etc
ሎት2፡- የፅዳት ማሽነሪዎች መለዋወጫ አቅርቦትና የጥገና አገልግሎት
ሎት3፡- የመኪና ግዥ (Mid - Bus, Double Pickup, Van mini bus)
ሎት4፡- ኢቪ ቻርጀሮች DC
ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ኤንቨሎፕ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እና ከሠዓት 7፡00-11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጠዋት 2፡00-6፡00) ማግኘት ይቻላል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ለሎት 2 ብር 50,000 ለሎት 1, 3 እና 4 ብር 100,000 ለእያንዳንዳቸው በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ጠዋት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የዕቃዎች ርክክብ የሚደረግበት ቦታ ገርጂ የድርጅቱ የዕቃ ግምጃ ቤት ይሆናል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ
ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 011-1-569992
አዲስ አበባ
