Tender Detail

Tender Details

  • Company በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
  • Address ደቡብ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0464570452
  • Website
  • Deadline22 Oct 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price50(ሃምሳ ብር)
  • Bid Security10,000(አስር ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ
  • opening dateበዕለቱ በ815 ደቂቃ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ በሳምንት ዕረፍት ወይም በህዝብ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  • Categories Consumable Goods , Stationery Materials

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ኮሬ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞኑ መምሪያ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በ2019 በጀት ዓመት የጽህፈት መሣሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ፋይናንስ መምሪያ


የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 1/2019

የጽህፈት መሳሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ኮሬ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞኑ መምሪያ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በ2019 በጀት ዓመት የጽህፈት መሣሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በጨረታ ለመሳተፍ ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች:-

  1. በዘርፍ ንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር ተከፍሎ የታደሰ፣ ቲን ቁጥር ሴርተፍኬት፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት የቫት ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ያለውና የሚያቀርብ፣
  2. ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ ኮሬ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ንብረት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር-8
  3. ተፈላጊ የጽህፈት መሳሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃዎችን የሚያቀርብበትን ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ ፕሮፎርማ ሞልቶ ከተፈላጊ መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ጋር በፖስታ አሽጎ የሚያቀርብ፣
  4. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 50/ሃምሳ ብር ብቻ/ ለኮሬ ዞን ገቢዎች ጽ/ቤት በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ሚያበቃበት ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከፋይናንስ መምሪያ ግዥና ንብረት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር-8 መውሰድ ይቻላል።
  5. ጨረታ ሣጥን የሚታሸግበትና የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በተመለከተ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ወደ ፊት የሚቆጠር በ16ኛው ቀን በ8:00 ሰዓት ታሽገው በዕለቱ በ815 ደቂቃ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ በሳምንት ዕረፍት ወይም በህዝብ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  6. የጨረታ አሸናፊ አሸናፊነት ይፋ ከሆነበት ዕለት ጀምሮ ለ5 የሥራ ቀናት ለቅሬታ አቤቱታ ጊዜ ሰጥቶ ከ8ኛው እስከ 15ኛው ቀን ድረስ የጠቅላላ ዋጋ 10 % የውል ማስከበሪያ ይዞ በመቅረብ ውል ካልተፈራረመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ ለመንግስት ውርስ በማድረግ ለአፈፃፀሙ ለክልል ግዥ ኤጀንሲ ሪፖርት እናደርጋለን።
  7. የጨረታ ማስከበሪያ 10,000/አስር ሺህ ብር ብቻ/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ የሚያስይዙ መሆን አለበት።
  8. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃዎችን ሁሉንም ወጪ ችሎ እስከ ኮሬ ዞን ፋይናንስ መምሪያ መጋዘን ድረስ አቅርቦ ማስረከብ አለበት።
  9. በጨረታ ሰነድ ላይ ናሙና የሚጠየቁትን ዕቃዎችንና ሌሎችም ያልተጠየቁትንም ኦርጅናልና 1ኛ ደረጃ ትክክለኛ ማቅረብ አለበት።
  10. ተጫራቾች ተሟልተው ያለመገኘት የጨረታ ሂደትን አያስተጓጉልም፣
  11. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ በጥራት 1ኛ ደረጃ መሆን አለበት። አቀላቅሎ የሚያቀርብ ካለ እንደ ተጭበረበረ ተቆጥሮ በክልል ግዥ ኤጀንሲና በህግ ርምጃ እንዲወሰድበት ይደረጋል።
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።

ለበለጠ መረጃ:-0464570452/ 0916056039

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

✨ messages.ai_summary
Kore Zone Finance Department seeks to procure stationery and other consumable goods for zonal sector offices via open tender. Bidders must have a valid trade license, renewed tax payment, TIN, commercial registration, supplier registration, and VAT registration. Items must be delivered to the Kore Zone Finance Department warehouse.
Save Tender