የ2018 ዓ.ም የሒሳብ ሰነዶች ኦዲት ሥራ - ማዕዶት በሱስ የተጎዱ ወጣቶች ማህበር
ማዕዶት በሱስ የተጎዱ ወጣቶች ማህበር
ግልፅ የኦዲት ሥራ
ጨረታ ማስታወቂያ
ማዕዶት በሱስ የተጎዱ ወጣቶች ማህበር ከመስከረም 28/2017 ጀምሮ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 በምዝገባ ሰርተፍኬት ቁጥር 7468 ተመዝግቦ እውቅና የተሰጠው ሀገር በቀል ያለ ትርፍ የሚሰራ ማህበር ሲሆን በሱስ ምክንያት የተጎዱና በጎዳና ላይ የሚኖሩ ወጣቶችን በሕክምናና በሥነ-ልቦና ማገገሚያ ስራዎች ሁለንተናዊ በሆነ መንገድ በማቋቋም ወደ ተስተካከለና አምራች ሕይወት እንዲመለሱ ለማድረግ የተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡
ስለሆነም የ2018 ዓ.ም የማህበሩን የሒሳብ ሰነዶች ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል፤ ከዚህ በታች በተጠቀሱት መስፈርቶች መሠረት መስፈርቶቹን የሚያሟላ በግልፅ ጨረታ መወዳደር ይቻላል፡-
- ተወዳዳሪዎች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የታክስ ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተወዳዳሪዎች የኦዲት ማድረግ ፈቃድ ያላቸው መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ዋጋ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ3 ተከታታይ የሥራ ቀናት በሚገኘው የማህበሩ ቢሮ በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፤
- ተወዳዳሪዎች ሥራውን ሠርተው የሚያስረክቡበትን ቀን በጨረታው ማሸነፊያ ሰነድ ላይ መጥቀስ አለባቸው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ በአካል በመምጣት እና በስልክ ቁጥር በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።
ስልክ ቁጥር፡- 0913580810/0911863658
አድራሻችን፡- የማህበሩ ጊዜያዊ ቢሮ ሰባራ ባቡር፣ አናንያ ሆስፒታል ያለበት ህንፃ ውስጥ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16
ማዕዶት በሱስ የተጎዱ ወጣቶች ማህበር
✨ messages.ai_summary
Maedot Besu-Affected Youth Association seeks audit services for its 2018 fiscal year accounting documents via open tender. Eligible bidders must have a renewed business license, TIN, VAT registration, tax payment proof, and audit authorization.
Not stated in the notice: opening date, bid security, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
