የሱቅ ኪራይ (የተለያዩ መጠን ያላቸው 4 ሱቆች) ጨረታ ቁጥር EMC/OT/THBD/SHOPRENT/02/2019 - የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን
Ethiopian Mineral Corporation (የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን)
የሱቅ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር- - EMC/OT/THBD/SHOPRENT/02/2019
የኢትዮጵያ ማዕድን፣ ኮርፖሬሽን የተለያዩ መጠን (size) ያላቸውን በዋናው መሥሪያ ቤት የሚገኙ ሱቆችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
| ሎት | የዕቃው ዓይነት | ብዛት | ሱቁ የሚገኝበት ቦታ | የጨረታው መዝጊያ ቀን | ሰዓት | የጨረታው መክፈቻ ቀን | ሰዓት | ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ |
| 1 | የተለያዩ መጠን (size) ያላቸውን ሱቆች | 4 | አዲስ አበባ | 12/02/2019ዓ.ም | 4፡00 ጠዋት | 12/02/2019 ዓ.ም | 4፡30 ጠዋት | አ.አ ዋናው መሥሪያ ቤት |
ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ግዴታዎች (መመሪያዎች) :-
- የጨረታ ሠነዱን በዚህ ማስታወቂያ በስተመጨረሻ በተገለጸው በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ብሎክ 2፣ በሚገኘው የኮርፖሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት በግንባር በመገኘት የማይመለስ ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በሶፍት ኮፒ ( soft copy ) መግዛት ይችላሉ፤
- የጨረታ ሰነድ የገዙ ተጫራቾች ለኪራይ የተዘጋጁትን ሱቆች ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታውን ለመክፈት አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ ሱቆች በሚገኙበት ቦታዎች በአካል በመገኘት ኮርፖሬሽኑ በሚመድበው ሠራተኛ አስጎብኚነት መመልከት ይችላል፡፡ የሱቆቹ ብዛት እንደአስፈላጊነቱ ቁጥሩ ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል፤
- ተጫራቾች ለሚከራዩት ሱቆች ብር 20000.00( ሃያ ሺ ብር ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ብቻ ከጨረታ ሠነዱ ጋር በማያያዝ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሣጥኑ ውስጥ ከሰነዳቸው ጋር የማስገባት ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊ ለሆኑትና ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ሕጋዊ ባንክ ከሆነ በሚከፍሉት ዋጋ ውስጥ ሊታሰብላቸው ይችላል ወይም ለተሸነፉት ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊዎች ለሱቅ ኪራይ ቅድሚያ የሶስት ወራት የሚከፍሉ ይሆናል፡፡
- ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በላዩ ላይ ድርጅቶች ከሆኑ ማህተም ያረፈበት፣ የግለሰቦች ከሆኑ ደግሞ ስሳት ፊርማ በመፈም ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንን በተመለከተ ከላይ በሰንጠረዥ ዋናው መ/ቤት በተገለጸው ቀን እና ሰዓት መሰረት ከጠዋቱ በ4፡00 ታሽጎ ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4፡30 በዋናው መ/ቤት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለሚከራዩት ሱቆች ስፋት ካሬ ሜትር ዋጋ በቁጥርና በፊደል ስርዝ ድልዝ የሌለበት በግልጽ ሞልተው በታሸገው ኤንቬሎፕ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋ ማስቀመጥ የሚኖርባቸው ሲሆን ገዥ የሚሆነው የነጠላ ዋጋው ይሆናል፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0911622263 /ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተከራዮች ሱቆችን ለጌጣጌጥ፣ ለማእደን ውጤቶች፣ ለባህላዊ አልባሳት እና ቅርጻቅርጾች መሸጫ እንዲሁም ለሌሎች አገልግሎት የሚከራዩ ይሆናል፡፡ ከአልኮሆል መጠጥ ውጭ፤
አድራሻ፡- 22 ማዞሪያ አውራሪስ ሆቴል አጠገብ
ስልክ ቁጥር :- 251-09 11 62 22 63
የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Mineral Corporation invites bids to rent four shops of various sizes at its head office in Addis Ababa. Shops may be used for jewelry, mineral products, traditional clothing, sculptures, and other services except alcohol. Bidders must buy the tender document and submit bids in sealed envelopes.
