የደንብ ልብስ፣ የፅህፈትና የጽዳት መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የመኪና መለዋወጫና ጎማ፣ የመኪና ጥገና፣ የግንባታ መሳሪያዎች፣ የእጽዋት ዘር እና የእንስሳት ሕክምና መሳሪያዎች ግዥ - የምስራቅ ወለጋ ዞን ኤበንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
በምስራቅ ወለጋ ዞን የኤበንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምስራቅ ወለጋ ዞን የኤበንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለወረዳው ባለ በጀት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ደንብ ልብስ፣ አላቂ የፅህፈት እና የጽዳት መሳሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎችና ጎማዎች፣ የመኪና ጥገና፣ የግንባታ መሳሪያዎች፣ የእጽዋት ዘር እና የእንስሳት ሕክምና መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ ጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ማስረጃ
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ና ፍቃዱንም በዘመኑ የታደሰ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በቀረበው ዝርዝር ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ የሚችሉ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ወይም /TOT/ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና ግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ማቅረብ የሚችሉ።
- የአቅራቢነት ምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ከገቢዎች ባለስልጣን ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ።
- ያሸነፉበትን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ኤበንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ወስጥ ገቢ ማድረግ የሚችሉ።
- ጥራታቸውን የጠበቁ ዕቃዎችን ማቅረብ የሚችሉና ጥራት የሌላቸውን ዕቃዎችን መቀየር የሚችሉ።
- ለጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ በአንዱ ዘርፍ 5000.00 /አምስት ሺህ ብር/ ማስያዝ የሚችሉ፣ በጥቃቅንና አነስተኛ እንተርፕራይዝ አዋጅ መሰረት የተደራጁ ከሆነ ደግሞ ካደራጀው አካል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከኤበንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ከመ/ቤቱ የገዛውን የጨረታ ሰነድ ላይ የእያንዳንዱን ዕቃ ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) ወይም ቲኦቲ(TOT) ጨምሮ በመሙላት ዶክሜንቱን ፈርሞና ማህተም አድርጎ ምንም ሳያጓድል ዋናውን እና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታ በማሸግ በመጨረሻም ሁለቱን ፖስታ በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ በተዘጋጀለት የጨረታ ሰነድ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
- የጨረታው ሰነድ በ15ኛው ቀን በ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 1 በግልጽ ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም (በሌሉበት ይከፈታል)።
- ክፍያ የሚፈጸመው የታዘዘውን ዕቃ በሙሉ ገቢ ሲያደርግ ነው።
- መስሪያ ቤቱ ዕቃዎችን 20% ይጨምራል ወይም ይቀንሳል።
- መ/ቤቱ ከነቀምቴ ከተማ 138ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ 466ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ ማብራሪያ ኤበንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0910825636/ 0917244448 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል
በምስራቅ ወለጋ ዞን የኤበንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Procurement of uniforms, stationery, cleaning materials, electronics, furniture, vehicle spare parts and tires, vehicle maintenance, construction tools, plant seeds, and veterinary equipment for the Ebenatu District Finance Office. Bidders must hold a valid trade license, VAT/TOT and TIN registration, supplier registration, and tax payment proof.
