Tender Detail

Tender Details

  • Company ሚሊንየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address የካ ክ/ከተማ ወደ ኮተቤ በሚወስደው መንገድ በተለምዶ 02 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወደ ህዝብ ደህንነት በሚያስወጣው አስፋልት ከፍ ብሎ ወረዳ 10 አጠገብ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 668 34 63
  • Website
  • Deadline15 Oct 2026, 5:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300(ሶስት መቶ ብር)
  • Bid Securityበሎት (CPO): ሎት1 22,000 (1%)፤ ሎት2 20,000 (1%)፤ ሎት3 15,000 (2%)፤ ሎት4 22,000 (1.7%)፤ ሎት5 7,000 (1.5%)፤ ሎት6 8,000 (1%)
  • opening dateበ11ኛው የሥራ ቀን ከዋለ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 3:30 ሰዓት
  • Categories Furniture , Stationery Materials , Cloth And Shoes

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሚሊኒየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም ለመሥሪያ ቤቱ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ፡- ሎት1. የደንብ ልብስ ፤ ሎት2. የትምህርት አላቂ ዕቃዎች ፤ ሎት 3. የፅዳት ዕቃዎች፤ ሎት4. ቋሚ ዕቃ ፤ ሎት5. የስፖርት ዕቃዎች ፤ ሎት6. ልዩ ልዩ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ሚሊንየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2019

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሚሊኒየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም ለመሥሪያ ቤቱ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ፡- ሎት1. የደንብ ልብስ ፤ ሎት2. የትምህርት አላቂ ዕቃዎች ፤ ሎት 3. የፅዳት ዕቃዎች፤ ሎት4. ቋሚ ዕቃ ፤ ሎት5. የስፖርት ዕቃዎች ፤ ሎት6. ልዩ ልዩ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች የምታሟሉ በዘርፉ የተሰማራችሁ ሕጋዊ ነጋዴዎችን በጨረታ አወዳድረን በጥራት እና በዋጋ በማወዳደር አሸናፊ ከሆኑት ድርጅቶች ለመግዛት የምንፈልግ መሆኑን እያሳወቅን፡፡

  • ተጫራቾች የ2019 ዓ.ም የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  • የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የተሰጠው፡፡
  • ወቅታዊ የ2018 ዓ.ም የግብር ግዴታቸውን የተወጡና በጨረታው መሣተፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • በኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ሊስት (Supplier List) ውስጥ የተመዘገቡ፡፡
  • በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ የጨረታ ተሳትፎ ከገቢዎችና ጉምሩክ ጽ/ቤት ቀኑ ያላለፈበት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የሚሊኒየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ክፍል ከጠዋቱ 2:30-11:30 ሰዓት ድረስ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ሕጋዊ የድርጅት ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በሚገኘው የዕቃዎች ዝርዝር ላይ የእያንዳንዱን ዋጋ በመሙላት በ2 በታሸገ ኤንቨሎፕ ሰነዱን አሽገው ዋናውን እና ኮፒውን ለያይተው ጨረታው እስከሚያበቃበት 10ኛው ቀን እስከ 11:30 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ11ኛው የሥራ ቀን ከዋለ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 3:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ (ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉለውም)፡፡
  4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ የሚያቀርቡት የዕቃ አይነት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበት ሥልጣን ባለው አካል የተፈረመባቸው የተሟላ አድራሻቸውን የሚገልጽና ሕጋዊ ማህተም ያረፈበት ሊሆን ይገባል፡፡
  5. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ዋጋ ላይ የዋጋ ለውጥም ሆነ ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
  6. አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸለት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅሬታ ተጠብቆ ከ8-15 ቀን ውስጥ በተወዳደሩበት ዋጋ እና በቴክኒክ አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው በኋላ ቀርበ የውል ማስከበርያ 10% /አስር ፐርሰንት CPO/ ለግዢ ፈጻሚ አካል ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. በጨረታው ያሸነፈ ተጫራች ለአሸነፉቸው ዕቃዎች ውል ከተዋዋሉበት ቀን ጀምሮ በአስር የሥራ ቀናት ውስጥ በራሳቸው ትራንስፖርት የማስጫኛና ማውረጃ ወጪ በመክፈል በሚሊኒየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡ ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ተጫራቾች በጨረታ ለቀረቡት ዕቃዎች ሳምፕል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. ከጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅታችሁ የዋስትና ደብዳቤ ለምታመጡ ድርጅቶች በምትወዳደሩበት ዘርፍ የራሳችሁ ምርት (አምራች) መሆናችሁን የሚገልፅ መረጃ በማቅረብ በአመረታችሁት ዕቃ ላይ ብቻ የምትወዳደሩ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  11. ት/ቤቱ አሸናፊ ተጫራች ከመረጠ በኋላ በሚገዙት ዕቃዎች ብዛት እና መጠን ላይ እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 20% /ሃያ ፐርሰንት/ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የተጠቀሰውን ብር በመመሪያው መሰረት ከታወቀ ባንክ የጨረታ ማስከበሪያ በCPO በት/ቤቱ ስም በማሠራት ከጨረታው መከፈቻ ቀን እና ሰዓት በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ተ.ቁየግዥ አይነትሎትየጨረታ ማስከበሪያ0.5-2%
1የደንብ ልብስ122,0001%
2የትምህርትና የቢሮ አላቂ ዕቃዎች220,0001%
3የፅዳት ዕቃዎች315,0002%
4ቋሚ ዕቃ422,0001.7%
5የስፖርት ዕቃዎች57,0001.5%
6ልዩ ልዩ ዕቃዎች68,0001%

አድራሻ፡- በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሚሊኒየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አጠና ተራ ድልድይ ስር ወደ ፍሲጋስ በሚወስደው መንገድ 20 ሜትር ገባ ብሎ

ስልክ፡- 011-280-42-34/35

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሚሊኒየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Millennium General Secondary School seeks to buy uniforms, educational materials, cleaning supplies, furniture, sports equipment, and miscellaneous goods via open tender. Bidders may bid for all or some lots. Eligible suppliers must have a renewed business license, VAT registration, TIN, tax compliance proof, and be on the government supplier list. Samples required.
Save Tender