የብርሃን ጉዞ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም የተለያዩ ለትምህርት የሚውል አላቂ የጽህፈት መሳሪያ ፤አላቂ የፅዳት እቃ ፤ የህንፃ መሳሪያ ፤የስፖርት እቃ ፤የደንብ ልብስ ፤ኤሌክትሮኒክስ ፤የሙዚቃ መሳሪያዎች ፤ የህክምና እቃ ፤ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ፡፡
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የብርሃን ጉዞ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ት/ቤት
የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001
የብርሃን ጉዞ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም የተለያዩ ለትምህርት የሚውል አላቂ የጽህፈት መሳሪያ ፤አላቂ የፅዳት እቃ ፤ የህንፃ መሳሪያ ፤የስፖርት እቃ ፤የደንብ ልብስ ፤ኤሌክትሮኒክስ ፤የሙዚቃ መሳሪያዎች ፤ የህክምና እቃ ፤ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ የሚችል።
- በሚወዳደርበት የስራ ዘርፍ ህጋዊ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- የተጨማሪ የእሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውንና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው
- በኢፌዴሪ የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ አቅራቢነት የተመዘገበ ና ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ
- የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ በcpo በእያንዳንዱ ሎት ከሚያቀርበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ 2% ማቅረብ የሚችል
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በተገለፀ በ7 ቀን ውስጥ ውል መፈፀም እና 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ cpo ማስያዝ የሚችል
ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰአት የጨረታውን ሰነድ በት/ቤቱ ሂሳብ ክፍል ቢሮ ቁጥር 02 የማይመለስ ብር 300/ ሶስት መቶ ብር /በመክፈል መውሰድ ይችላሉ በተጨማሪም ሳምፕል እቃዎችን ቢሮ ቁጥር 06ማስገባት ይችላሉ ።
ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ጨረታ እቃ /ናሙና/ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው ናሙና ለማቅረብ በማይቻልባቸው እቃዎች በፎቶ ና ል ማግለጫ ናሙና ማቅረብ ይቻላል። ናሙና ካላቀረቡ ከጨረታ ውጪ ናቸው ። ተጫራቾች በተመረጠው ናሙና መሰረት በ7 ቀን ውስጥ እቃዎቹ በት/ቤቱ እቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች ሰነዱ ላይ የተጠቀሱትን እቃዎች የሚሸጥበትን ዋጋና ሌሎች መረጃዎች በታሸገ ሁለት ዋና ና ቅጂ ኤንቨሎፕ ላይ በተጠቀሰው መጨረሻው ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰአት ከ 2:30 እስከ 10:00 ለዚህ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ።
ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት መወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም። ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት ከጠዋቱ በ 4:30 ይከፈታል። መ/ቤቱ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብት አለው
አድራሻ፡- ካዝንቺስ እንደራሴ ከፍ ብሎ ብርሃን ጉዞ አ/ህ/መ/ደ/ት/ቤት
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0115329133/0115329132
