የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለቆሬ ዋር ኮሌጅ ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ዝርዝራቸው ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘ የስራ ዝርዝር (Specification) መሰረት የ Distribution Board ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Defense Construction Enterprise (የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/EM/136/2026
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለቆሬ ዋር ኮሌጅ ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ዝርዝራቸው ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘ የስራ ዝርዝር (Specification) መሰረት የ Distribution Board ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
| ተ.ቁ | የስራ ዝርዝር | የጨረታ ቁጥር | የጨረታ መዝጊያ ቀን | የጨረታ መክፈቻ ቀን |
| 1 | Distribution Board | DCE/EM/136/2026 | 11/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 4:00 | 11/02/2019ዓ.ም ከቀኑ 4:15 |
ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፤ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የታደሰ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሠነዱ በተጠቀሰው ብዛት እና ስፔስፊኬሽን መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ቃሊቲ ቶታል ዝቅ ብሎ የቀድሞ መ.ኮ.ድ ግቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋናው መስሪያ ቤት የግዥ እና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሠነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ጥቅምት 11/2019ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ጥቅምት 11/2019ዓ.ም ከጠዋቱ 4:15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ቡድን ቢሮ ይከፈታል፡፡
- አንድ ተጫራች ለአንድ ዕቃ መወዳደር የሚችለው በአንድ ዓይነት ሞዴል/ብራንድ/ ብቻ ነው ፤ በአማራጭ የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር ቁጥር 0114-40-34-34/33
ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72 WWW.dce-et.com/Email:-info@dce-et.com
ቃሊቲ ቶታል ዝቅ ብሎ የቀድሞ መኮድ ግቢ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
✨ messages.ai_summary
Defense Construction Enterprise seeks bidders to supply Distribution Boards for the Kore War College construction project, per the tender document's specification. Eligible bidders must be active in the sector with a valid renewed business license, tax payments, VAT registration, and renewed tax clearance.
