በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጌዴኦ ዞን የኮቾሬ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለኮቾሬ ወረዳ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች በሎት 1 የጽሕፈት መሣሪያዎችና ለሎሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን በሎት 2 የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጌዴኦ ዞን የኮቾሬ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 002/2019
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጌዴኦ ዞን የኮቾሬ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለኮቾሬ ወረዳ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች በሎት 1 የጽሕፈት መሣሪያዎችና ለሎሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን በሎት 2 የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡-
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡-
- ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑ
- የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡-
- የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡-
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ 50,000/ሃምሳ ሺህ/ ብር ማስያዝ የሚችል ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኮ/ወ/ፋይናንስ ስም አሰርተው ማቅረብ የሚችል፡-
- የጨረታ ሠነድ በማይመለስ 200/ ሁለት መቶ / ብር መግዛት የሚችሉ፡-
- ከአሠሪ መሥሪያ ቤት ጋር በሚገባው ውል መሠረት በጨረታ ያሸነፉትን ንብረት እስከ ኮቾሬ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት መጋዘን ድረስ ካስረከቡ በኋላ ሙሉ ክፍያውን መረከብ የሚችሉ፡፡
- የግዥው መጠን ከ ሃያ ሺህ ብር በላይ ከሆነ መ/ቤቱ የቫቱን ግማሽ ፐርሰንት ቀርጦ የሚያስቀር መሆኑ ይታወቅ፡-
- አሸናፊው ውል ገብቶ ወደ ሥራ ከመግባቱ በፊት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሠነድ በኮቾሬ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት የግዥ ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 01 ከ26/01/2019 ዓ.ም እስከ 16/02/2019 ዓ.ም ድረስ እየተሸጠ ቆይቶ በ16 ኛው የሥራ ቀን ላይ በ17/02/2019 ዓ.ም ዕለተ ማክሰኞ ከረፋዱ 05:00 ሰዓት ላይ የመጫረቻ ሠነድ ኦርጂናሉንና የማይመለስ አንድ ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እናት/ፖስታ ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ገብቶ በዕለቱ ከረፋዱ 05:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልጽ ይከፈታል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 046-366-0433/+251916920261 +251916634937
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጌዴኦ ዞን የኮቾሬ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Kochore Woreda Finance and Plan Office invites bids for Lot 1: stationery and consumable office supplies, and Lot 2: office electronics, for sector offices. Bidders must have a valid license, tax and VAT registration, supplier certificate, and deliver goods to the office warehouse.
