የመድሃኒት እና ሬጀንት፣ የግንባታ እቃ፣ የፅህፈት መሳሪያ፣ የፅዳት፣ የውሀ እና የሙብራት እቃ ግዥ - የኦለንጭቲ ሆስፒታል (ምስራቅ ሸዋ ዞን)
በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳ የኦለንጭቲ ሆስፒታል
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የኦለንጪቲ ሆስፒታል
በምሥ/ሸዋ ዞን ኦለንጭቲ ሆስፒታል በ 2019 በጀት ዓመት የመድሃኒት እና ሬጀንት የግንባታ እቃ፤የፅህፈት መሳሪያ (እስቴሽነሪ)፤ የፅዳት እቃ የውሀ እቃና የሙብራት እቃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም እጩ ተጫራቾች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
በመሆኑም ከላይ በተጠቀሱት ላይ ህጋዊ ፍቃድ ያላችሁና ያሳደሳችሁ የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ማቅረብ የምትችሉ 5,000 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO በማስያዝ በተገለፀው ቀን መወዳደር ይኖርባቸዋል።
ማሳሰቢያ
- በመድሃኒት እና በሬጀንት ላይ ለምትወዳደሩ 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባችኋል።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን ማህተማቸውን ና አድራሻቸውን መጻፍ ይኖርባቸዋል፡፡(ሰነዱ በተለያየ ፖስታ ኦርጂናል እና ኮፒ መቅረብ አለበት፡፡
- ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች ከሆስፒታሉ ግዢና ፋይናንስ የስራ ሂደት ክፍል ዘውትር በስራ ሰዓት 200 ብር (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ ።
- ጨረታው የሚከፈተው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የስራ ቀን አየር ላይ ውሎ በ አስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ላይ ተዘግቶ በዚያው ቀን ተጫራቾቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት 8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡
- ዋጋ ስትሞሉ ከቫት ጋር መሙላት ይኖርባችኋል፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጫረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ
በስልክ ቁጥር 0915930940/ 0931527083,0919209295
በኦሮሚያ ጤና ቢሮ የምስራቅ ሸዋ ዞን
ጤና ጽ/ቤት የኦለንጭት ሆስፒታል
✨ messages.ai_summary
Olenchiti Hospital seeks suppliers for pharmaceuticals and reagents, construction materials, stationery, cleaning, water, and plumbing supplies. Eligible bidders must hold valid licenses, be tax-compliant, and submit signed, stamped documents in separate original and copy envelopes. Partial or full cancellation is reserved.
