Tender Detail

Tender Details

  • Company የአንዶዴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address ሰሚት ጤና ጣቢያ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-8-93-16-37
  • Website
  • Deadline15 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceበየሎቱ የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር)
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateበ11ኛው ቀን 4:30 ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል
  • Categories Cleaning & Janitorial , Textile, Garment & Leather , Machinery

የደንብ ልብስ፣ የፅዳት፣ የቢሮና የትምህርት ዕቃዎች፣ ፕላንትና ማሽነሪ መሳሪያ ግዥ እና የጥገና አገልግሎቶች (11 ሎቶች) - የአንዶዴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

የአንዶዴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የመለያ ቁጥር 01 /2019 ዓ/ም

ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አስተዳደር የአንዶዴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ለ2019 ዓ/ም በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከህጋዊ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው::

ሎት1የደንብ ልብስ32,000
ሎት2አላቂ የፅዳት ዕቃ21,000
ሎት3አላቂ የቢሮ ዕቃ13,000
ሎት4ኮምፒውተር ፎቶ ኮፒ ጥገና7,000
ሎት5ህትመት ባነር2,000
ሎት6አላቂ የትምህርት ዕቃ12,000
ሎት7አላቂ ህክምና ዕቃዎች4,000
ሎት8የደንብ ልብስ ማሰፊያ2,000
ሎት9ፕላንት እና ማሽነሪ መሳሪያ መግዣ40,000
ሎት10ልዩ ልዩ መሳሪያዎች6,000
ሎት11ለህንጻና ለቁሳቁስ እና ተገጣጣሚዎች እድሣትና ጥገና13,000
  1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የግብር መለያ ቁጥር (TIN No) ካሽ ሪሴስተር ተመዝጋቢ የሆኑ / ያለው ብቻ ነው::
  2. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑበት እና የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
  3. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር1-2 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በታሸገ ኤንቨሎፕ ከዋጋ ማቅረቢያ ኦርጅናል ሰነድ እና ኮፒ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::ይህም ህጋዊ ሠነድ እና የዋጋ ማቅረቢያ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት::
  4. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 02 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ::
  5. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው በዓየር ላይ ከፍት ሆኖ የሚቆየው ለ10(ለአስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከአንዶዴ 2ኛ ደረጃ/ት/ቤት ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ መግዛት ይችላሉ::
  6. የሚወዳደሩበትን ዋጋ ከት/ቤቱ ከገዙት በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሰነድ ላይ ሞልተው ከላይ በተራ ቁጥር አራት በተገለፀው መሰረት ጨረታው በአየር ላይ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ በስራ ሰዓት በአንዶዴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ባዘጋጀነው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
  7. የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ በዋለ 11 / በአስራ አንደኛው / ቀን ከጠዋቱ 4:00 ታሽጎ ተመልሶ 4:30 የሚከፈት ሲሆን ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ::
  8. የጨረታው መከፈቻ ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል::
  9. ተጫራቾች ያሸነፉአቸውን ዕቃዎች የግዥ መጠየቂያ (purchese order) ከደረሳቸው ቀን ጀምሮ 5 (አምስት) ቀናት እስከ መስሪያ ቤቱ መጋዘን ድረስ እቃውን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው::
  10. ተጫራቾች ናሙና ለሚጠይቁ እቃዎች ናሙና ማቅረብ እና እቃዎችን በዝርዝር መግለጫዎች በማያያዝ ማቅረብ ይችላሉ::
  11. ተጫራቾች የተሞላው የጨረታ ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ45 (አርባ አምስት) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል::
  12. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ10%(አስር በመቶ ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማስያዣ ሲፒኦ የጨረታ ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
  13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ መሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  14. መስሪያ ቤቱ ለጨረታ ባቀረበው ዕቃ ውሉ ሳይቀየር 20% መቀነስም ሆነ መጨመር ይችላል::

ለበለጠ መረጃ በአካል በአንዶዴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሰሚት ጤና ጣቢያ ፊት ለፊት በመምጣት ፋይናንስ አስተዳደር በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ::

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አስተዳደር የአንዶዴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Andode Second Cycle School invites legal suppliers to bid for uniforms, cleaning, office and educational materials, plant and machinery equipment, and maintenance services across 11 lots. Bidders must hold a valid trade licence, TIN, cash register receipt, VAT registration, and supplier certificate.
Not stated in the notice: bid security. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender