Tender Detail

Tender Details

  • Company ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ
  • Address , Phone: ..........
  • Website
  • Deadline19 Oct 2026, 2:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500
  • Bid Security200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና
  • opening dateበዛው እለት 8:30 ላይ ይከፈታል
  • Categories Spare Parts , Vehicle Spare Parts

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ የተለያዩ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር Gada/NCB/01/2019

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ የተለያዩ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታዉ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በሚሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. በዘርፉ የተሰማሩ ፤የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ እንዲሁም ንግድ ምዝገባ ምስክር እና ሌሎች አስፈላጊዉን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  2. ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቅያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚዉል ሲሆን ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 11:00 በመምጣት የማይመለስ 500 (አምስትመቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
  3. ማንኛዉም ተጫራች በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ ከብ ማህተም በማድረግ እና በመፈርም በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ያለባቸዉ ሲሆን የሞሉትን ጨረታ ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለያዩ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው
  5. የጨረታ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት የዋጋውን ውል ማስከበሪያ 10 % በማስያዝ ውል መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መግቢያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና እራሳቸውን ከጨረታ ማግለል አይቻልም
  7. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተረሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም
  8. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰረዘ እና የተደለዘ ሆኖ ለመለየት የሚያስቸግር ዋጋ ተቀባይነት የለውም
  9. ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል እንደተፈጸመ ተመላሽ ይሆናል፡፡
  10. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቅያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛዉ ቀን በ8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት 8:30 ላይ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  11. የጨረታ መከፈቻ ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  12. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

አድራሻ፡- ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-558-25-19/0909273110

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ

✨ messages.ai_summary
Gada Transport and Logistics PLC seeks to buy various dry cargo vehicle spare parts through open national competitive bidding. Eligible bidders must be engaged in the sector, tax-compliant, and hold a renewed business license and commercial registration.
Save Tender