Tender Detail

Tender Details

  • Company በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የአለም ባንክ ጤና ጣቢያ
  • Address ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የአለም ባንክ ጤና ጣቢያ ልዩ ቦታ ትሮፒካል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጀርባ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0118-32-59-69
  • Website
  • Deadline19 Oct 2026, 9:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Securityበሎት: ከብር 5,000.00 እስከ 50,000.00 (CPO)
  • opening dateጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት በ11ኛ ቀን በ3:30 ሰዓት ታሽጎ 4:00 ሰዓት ላይ
  • Categories Pharmaceutical Products , Medical Equipment And Supplies , Electronics Materials

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኘው የአለም ባንክ ጤና ጣቢያ ለ2019 ዓ.ም ሁለተኛ ዙር ጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የአለም ባንክ ጤና ጣቢያ


የጨረታ ማስታወቂያ

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኘው የአለም ባንክ ጤና ጣቢያ ለ2019 ዓ.ም ሁለተኛ ዙር ጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተ.ቁየአገልግሎት አይነቶችሎትየጨረታ ማስከበሪያ
1የፅዳት እቃዎች15,000.00
2የጥገና እቃዎች215,000.00
3የደንብ ልብስ315,000.00
4ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ እቃ ግዥ420,000.00
5የህክምና እቃዎች ጥገና አገልግሎት ግዥ520,000.00
6የመድኃኒት እና የላብራቶሪ ሬጀንት ግዥ650,000.00
7የሕክምና ክፍሎች በር ግዥ75,000.00
8የተለያዩ አላቂ የቢሮ እቃዎች
የጽሕፈት መሣሪያዎች
85,000.00
9የኮምፒዩተር ፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ጥገና አገልግሎት95,000.00
10አውቶክሌቭ መቀየሪያ እቃ ግዥ105,000.00

ስለሆነም መወዳደር የምትፈልጉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ።

  1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ ምዝገባ ያላቸው፣ የዘመኑ ግብር ለመክፈላቸው ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ አቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ፣ 6ወር ያልሞላው ከሊራንስ ማስያዝ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. አነስተኛ ጥቃቅን ተቋማት በአዋጁ መሰረት የተቋቋሙ አምራች በሆኑበት ዘርፍ ብቻ ወይም በሚያመርቱት እቃ ብቻ ከደራጃቸው አካል በሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ መወዳደር ይችላሉ። ቋማት አምራች ባልሆኑበት ዘርፍ በዋስትና ደብዳቤ አናስተናግድም።
  3. የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 200.00/ሁለት መቶ ብር/ብቻ በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከ2:30-11:30 በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 7 መውሰድ ይቻላል።
  4. ከላይ በተገለጸው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ በአለም ባንክ ጤና ጣቢያ ስም በታወቀ ባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የሰሩትን ሰነድ የሚወዳደሩበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ በመሙላት በየሎቱ ኦሪጅናሉንና ኮፒውን በሁለት ፖስታ አሽገው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 /አስር/ የሥራ ተከታታይ ቀናቶች እና በ11ኛ ቀን 3:30 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሁሉንም እቃ ናሙና /ሳምፕል /ማንዋል/ ፎቶግራፍ/ ማቅረብ አለባቸው።
  7. ተጫራቾች ከገዙት ጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልቶ የሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
  8. ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት በ11ኛ ቀን በ3:30 ሰዓት ታሽጎ 4:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አለም ባንክ ጤና ጣቢያ በግልጽ ይከፈታል።
  9. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጮች ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ለጨረታ የቀረበ ሳምፕል ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ በሁለት ወር ውስጥ ሳንገሉን ካልወሰዱ ለተቋሙ ገቢ ይደረጋል።
  11. በሎት 7 እና 10 ሳምፕል በካታሎግ ወይም በፎቶግራፍ አትሞ በሚያሳይ ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  12. ማንኛውም ተጫራች ናሙና ሲያመጡ በካርቶን ወይም በማዳበሪያ አሽጎ ማቅረብ አለባቸው። በፌስታል የሚመጣ ናሙና ተቀባይነት የለውም።
  13. ተጫራቾች የሰሩትን የጨረታ መመሪያ ሰነድ በየገጹ ፊርማው ክብ ማህተም በማድረግ ከኦሪጅናል ሰነድ ጋር በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  14. እቃውን በሚያመጡበት ሰዓት ንብረት ክፍል ከቀኑ 10:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት አለባቸው።

አድራሻ፡- በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የአለም ባንክ ጤና ጣቢያ
ልዩ ቦታ ትሮፒካል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጀርባ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 01113693703

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የአለም ባንክ ጤና ጣቢያ

✨ messages.ai_summary
Alem Bank Health Station seeks suppliers for cleaning materials, maintenance items, uniforms, electronics, medical equipment repair, medicines and lab reagents, doors, office supplies, printer/photocopy repair, and autoclave parts. Bidders must have a valid license, tax registration, supplier listing, and VAT registration. Samples required.
Save Tender