Tender Detail

Tender Details

  • Company South Ethiopia Regional State Transport and Road Development Bureau (የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ)
  • Address ዲላ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0461316004
  • Website
  • Deadline17 Oct 2026, 5:30 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Securityብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ (CPO ወይም ባንክ ጋራንቲ)
  • opening dateበ16ኛው ቀን 4:30 ላይ ይከፈታል (16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት)
  • Categories Computer Laptop And Accessories , Office Machines And Computers , Electronics Materials

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የትራንስፖርትና መንገድ ልማት አስተዳደር ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ማለትም ዲስክቶፕ ኮምፒውተር ላፕቶፕ cor 15 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

South Ethiopia Regional State Transport and Road Development Bureau (የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ)


የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2019

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የትራንስፖርትና መንገድ ልማት አስተዳደር ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ማለትም ዲስክቶፕ ኮምፒውተር ላፕቶፕ cor 15 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ቫት ተመዝጋቢ የሆነ አመታዊ የስራ ግብር የከፈሉበትን፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ አያይዘው ጨረታ ሰነድ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የእቃዎችን ዝርዝር እስፔስፊኬሽንና የጨረታ ሰነድ ቢሮ ቁጥር 17 ድረስ መጥተው የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 አስራ አምስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው ቀን 4:30 ላይ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO/ ወይም ባንክ ጋራንቲ በቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ ውስጥ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቴክኒካል አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ፥ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ እያንዳንዳቸውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እና ጠቅላላውን በአንድ በእናት ፖስታ ታሽጎ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 11፡30 ድረስ ቢሮው ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  6. ተጨማሪ መረጃ ከሰነዱ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እያሳወቅን የደቡብ አ/ክ መንግስት የትራንስፖርትና መንገድ ልማት አስተዳደር ቢሮ እንደገና ተሻሽሎ የወጣው የግዢ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 282017 እና መመሪያው ላይ የተደረገውን ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ሰርኩላር ተፈጻሚ ይደረጋል።

-ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ ማብራሪያ፡ በስልክ ቁጥር 0916029511/0913725758 መደወል ይችላሉ።

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የትራንስፖርትና መንገድ ልማት አስተዳደር ቢሮ

✨ messages.ai_summary
South Ethiopia Regional State Transport and Road Development Bureau seeks to buy desktop computers and laptops (core 15) via open tender. Bidders need a renewed trade license, VAT registration, tax payment proof, supplier certificate, VAT certificate, and TIN copy.
Save Tender