Tender Detail

Tender Details

  • Company Semera Customs Branch Office (ሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)
  • Address ሰመራ ፡ አፋር ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 033 366 2302
  • Websitehttp://www.ecc.gov.et/
  • Deadline08 Oct 2026, 9:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100(አንድ መቶ ብር)
  • Bid Securityግልጽ ጨረታ: የሰጡትን ዋጋ 5%; ሐራጅ ጨረታ: በምድብ ከብር 10,000 እስከ 200,000 (CPO)
  • opening dateግልጽ ጨረታ: በዚያው ቀን (28/01/2019) 3:45 ሰዓት ይከፈታል; ሐራጅ ጨረታ: 28/01/2019 ዓ/ም 4:00 ሰዓት ይከፈታል
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Electronics Materials , Cloth And Shoes

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለጹ የተለያዩ የተወረሱ ዕቃዎችን በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ጨ.ቁ 03/2019 ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Semera Customs Branch Office (ሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)


የጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለጹ የተለያዩ የተወረሱ ዕቃዎችን በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ጨ.ቁ 03/2019 ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

ተ.ቁዘርፍየጨረታው ዓይነትእቃው ያለበት ቦታ
1.ኤሌክትሮኒክስግልፅ ጨረታበሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግስት መጋዘን
2.ኮስሞቲክስግልፅ ጨረታበሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግስት መጋዘን
3.ጫማግልፅ ጨረታበሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግስት መጋዘን
4.የእጅ ሰዓቶችግልፅ ጨረታበሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግስት መጋዘን
5.ልዩ ልዩ ዕቃዎችሐራጅ ጨረታበሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግስት መጋዘን
6.ፓኪንግ ማሽንሐራጅ ጨረታበሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግስት መጋዘን
7.መለዋወጫዎችሐራጅ ጨረታበሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግስት መጋዘን
8.ጫማሐራጅ ጨረታበሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግስት መጋዘን
9.ኤሌክትሮኒክስሐራጅ ጨረታበሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግስት መጋዘን

በመሆኑም ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን::

  1. በጨረታው ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ) ማቅረብ ያለበት ሲሆን የሚወዳደሩበት የጨረታ ዓይነት መነሻ መሸጫ ዋጋው ከብር 500 ሺ በታች የሆነ ማንኛውም እቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ አያስፈልገውም:: በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ያለበት ሲሆን ለሐራጅ ጨረታ ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች በጨረታ መከፈቻው ቀንና ሰዓት ማቅረብ ይኖርበታል፤
  2. የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ1:00-5:00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በመገኘት ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ግቢ ውስጥ የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 በመምጣት መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን::
  3. ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና በሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው መለዋወጫዎች ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር) ጫማ (ምድብ 01) ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር)፤ጫማ (ምድብ 02) ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር)፣ ኤሌክትሮኒክስ 20,000 (ሃያ ሺ ብር)፣ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ብር 10,000 (አስር ሺ ብር) እና ፓኪንግ ማሽን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር) ለጨረታ ዋስትና(CPO) በቅ/ጽ/ቤቱ ስም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION SEMERA BRANCH OFFICE በሚል በባንክ አሰርተው ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰመራ እና ከሎጊያ ቅርንጫፎች ብቻ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል::
  4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ::
ተ.ቁየቅ/ጽ/ቤቱ ስምየጨረታው አይነትየንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮየጨረታው መዝጊያ እና መከፈቻ ቀንና ሰዓት
1.ሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤትግልጽ ጨረታእስከ 27/01/201928/01/2019 ዓ.ም 3:30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 3:45 ሰዓት ይከፈታል
2.ሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤትሐራጅ ጨረታእስከ 27/01/201928/01/2019 ዓ/ም 4:00 ሰዓት ይከፈታል

5. ጨረታው መከፈቻ ቦታ:- በሰመራ : ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል::

6. ተጫራቾች ያስያዙትን ዋስትና (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል::

7. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሜ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን የእቃውን ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል:: ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል::

8. ቅ/ጽ/ቤቱ ለጨረታ የቀረበውን እቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ - ሙሉ መብት አለው::

7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

8. አሸናፊ ተጫራች ተጨማሪ እሴት ታክስ (vat) 15% የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ::

9. ለተጨማሪ መረጃ በስ/ቁ:- 0332401510 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::

የሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Customs Commission's Semera branch invites bids to sell confiscated goods: electronics, cosmetics, shoes, watches, assorted items, packaging machine and spare parts, via open and auction tender. Bidders need a valid trade licence, VAT registration, TIN and tax clearance; VAT certificate not required for items under 500,000 birr.
Save Tender