Tender Detail

Tender Details

  • Company በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በደዋ ጨፋ ወረዳ አስተዳደር የወለዲ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት
  • Address , Phone: 0913686688
  • Website
  • Deadline07 Oct 2026, 10:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00 (አራትመቶ ብር)
  • Bid Securityከጠቅላላ የጨረታ መጠን 10% (በጥሬ ገንዘብ ወይም CPO)
  • opening date27/01/2019 ዓ/ም 4፡40
  • Categories Building Materials

በአብክመ የኦሮ/ብ/ዞን የደዋ ጨፋ ወረዳ ወለዲ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በግልፅ ጨረታ ለኮሪደር ልማት ስራ የሚሆን 3000 ካሬ ቴራዞ አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል።

በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በደዋ ጨፋ ወረዳ አስተዳደር የወለዲ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ የኦሮ/ብ/ዞን የደዋ ጨፋ ወረዳ ወለዲ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በከተማው ውስጥ እያሰራ ላለው የኮሪደር ልማት ስራ የሚሆን 3000 ካሬ ቴራዞ በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ከአሸናፊዎች መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን መስፈርቶቹም፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የምዝገባ የምስክር ወረቀት (Tin No) አብረው ማያያዝ የሚችሉና ከ 50,000 ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ የያዘ ከኦሮ/ብ/ዞ/ደ/ጨ/ወ/ ወለዲ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ ቁጥር 02 በመቅረብ ከ 20/01/2019 ዓ/ም የማይመለስ 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ለ7 /ሰባት/ ተከታታይ ቀናት ገዝተው በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ /ኢንቨሎፕ/ በማሸግ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ በ8ኛው ቀን ማለትም በ27/01/2019 ዓ/ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 4፡30 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡40 የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን ሆኖም የመክፈቻው ዕለት ባዕላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለዉ የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች ለሞሉት ለጠቅላላ የጨረታ መጠን ላይ 10%/ፐርሰንት/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት መረጃ ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ለበለጠ መረጃ የተጫራቾችን መመሪያ ላይ መረዳት ይቻላል ወይም በስልክ ቁ.0941827356/0965076512 /0922926135 መደወልና መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  7. አሸናፊዎች ያሸነፉትን እቃ ደዋ ጨፋ ወረዳ ወለዲ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ በጨረታ አሸናፊ የሆኑት ተጫራቾች ዉል ካልገቡ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ በሙሉ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  8. መ/ቤቱ ጨረታዉን በሎት ያወዳድራል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በአብክመ የኦሮ/ብ/ዞን የደዋ ጨፋ ወረዳ ወለዲ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት

✨ messages.ai_summary
Woledi Town Municipality seeks to procure 3,000 square meters of terrazzo for its corridor development project via open tender. Bidders must hold a valid trade license, attach a TIN certificate, and register for VAT if above 50,000 birr. Winners must deliver materials to the municipality.
Save Tender