Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline15 Oct 2026, 10:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00 (ሁለትመቶ ብር)
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን በየሎቱ ይለያያል።
  • opening dateጥቅምት 05 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 5፡00 ሰዓት
  • Categories Rent , Land, House, Building And Warehouse Rent

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ SSNT-T644 በድጋሚ በወጣ ግልፅ ጨረታ በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል Phase I ሕንፃ ውስጥ የሚገኙ 2 ሱቆች፣ የጌጣጌጥ/የከበረ ድንጋይ መሸጫ እና የምርት ማሳያ ቦታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- SSNT-T644

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ- በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል Phase I ሕንፃ ውስጥ የሚገኙ 3 የተለያዩ ቦታዎች ላይ ለምርት ማሳያ ቦታ፣ ጌጣጌጥ ወይም የከበረ ድንጋይ መሸጫ እና 2 ሱቆች የሚፈለጉትን ምርት ወይም አገልግሎት መስጫ የሚውሉ ባዶ ቦታዎችን በኪራይ መስራት የሚፈልጉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች በሆቴል እንግዶች ሊፈለጉ የሚችሉ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በሆቴሉ ግቢ ውስጥ የማይገኙ ሌሎች ምርቶችና አገልግሎቶች ላይ የተሰማሩ መሆን አለባቸው። (የቆዳ ምርቶች፣ ብሔራዊ/ባህላዊ ቀሚሶች፣ የቡቲክ ሱቆች፣ የመጽሐፍ መደብሮች፣ የቡና ምርት ሱቆች፣ ከቀረጥ ነፃ ሱቆች፣ ባንኮች፣ የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች፣ የመዋቢያ ሱቆች፣ የቆዳ እንክብካቤ ሱቆች፣ የውበት ሳሎኖች፣ የመኪና ኪራይ ቢሮዎች፣ ከሆቴል ጋር የተያያዙ ማናቸውም ምርቶችና አገልግሎቶች መሆን የለባቸውም)።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

  1. ተጫራቾች ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል በዘርፉ ለመስራት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ የሚያገለግል ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆንይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር/ሁለት መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T644 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy)፣ የጨረታውን ቁጥርና አይነት እንዲሁም የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።
  3. በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid security) አንድ መቶ ሺ ብር (ብር 100,000) ለሁለቱ ሱቆች (ሱቅ 3 እና 5)፣ አንድ መቶ ሺ ብር (ብር 100,000) ለጌጣጌጥ ወይም የከበረ ድንጋይ መሸጫ ሱቅ እና ሀያ አምስት ሺ ብር (ብር 25,000.00) ለምርት ማሳያ አገልግሎት የሚውል ቦታ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ ይኖርበታል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ ተቋም የተገኘ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
  4. ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 120 ቀናት የሚቆይ ይሆናል። አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው።

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በተለያየ ኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል ጥቅምት 05 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ጠዋት 4፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ጠዋት 5፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል

ስልክ ቁጥር 011-517-8953

ወ/ሮ ጠይሚ ተሰጋ

ኢ-ሜይል: TeymeT@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Airlines Group invites bids to rent three vacant spaces at Ethiopian Skylight Hotel Phase I: two shops and one jewelry/precious stone sales or product display area. Bidders must be engaged in products/services not currently available at the hotel, excluding leather goods, cultural dresses, boutiques, bookstores, coffee shops, duty-free shops, banks, forex bureaus, cosmetics, beauty salons, and car rental offices.
Save Tender