የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ የተለያዩ የመበየጃ ኤሌክትሮድ ግልፅ ጨረታ (ቁጥር ሙሲፋ/01/2019)
Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory (በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ)
የሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ
ቁጥር ሙሲፋ/01/2019
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የመበየጃ ኤሌክትሮድ በገልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የ2018/2019 ዓ/ም የተጨማሪእሴት ታክስምዝገባሰርተፍኬት የታክስከፋይ ምዝገባሰርተፍኬት እና ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት ገርጂ የቀድሞው ኤምፔሪያል ህንፃ ከሚገኘው የፋብሪካው የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (C.P.O) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዕለቱ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡ ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ ሙብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
