የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ በ2019 የበጀት ዓ.ም ለሰልጣኞች ምግብ አገልግሎት የሚውል የስጋ በሬ፣ ለመኪናዎች ሰርቪስ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ የውሃ እቃዎች፣ የመብራት እቃዎች እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Oromia Police College (የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ)
የግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ኦፖኮ/02/2019
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ በ2019 የበጀት ዓ.ም ለሰልጣኞች ምግብ አገልግሎት የሚውል የስጋ በሬ፣ ለመኪናዎች ሰርቪስ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ የውሃ እቃዎች፣ የመብራት እቃዎች እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ተጫራቾች ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ አዳማ በሚገኘው የጨረታውን ሰነድ በመግዛት ጨረታው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ለመወዳደር የምትፈልጉ ድርጅቶች፣ ነጋዴዎች/አቅራቢዎች፡-
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የ2018/2019 ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት መረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የሥራ ግብር ከፋይ መሆኑን የሚገልፅ የቲን ቁጥር መረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የአቅራቢዎች ስም ዝርዝር (Supply List) ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልፅ መረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ግብር መክፈላቸውን የሚገልፅ መረጃ (ክሊራንስ) ማቅረብ የሚችል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT 15%) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚገልፅ መረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለውድድር ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ (CPO) 2% ከጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ አሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱ የተዘጋጀው በኦሮምኛ ቋንቋ ስለሆነ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ ሊዩ ሊዩ ገቢዎች በሚለው ስም A/C ቁጥር 1000133792817 ላይ በማስገባት የጨረታ ሰነዱን በኮሌጅ ቁጥር ገቢ ፋይናንስ ቢሮ በማቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በተናጥል በፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታው ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እሁድን ሳይጨምር ለ10(አስር) ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን እስከ 5:30 ሰዓት ተሽጦ የጨረታው ሰነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ በዚሁ ዕለት ሳጥኑ ከቀኑ 6:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን ከሰዓት በኋላ በ8:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ በኮሌጁ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- ኮሌጁ በሚገዛው ማንኛውም እቃ ላይ 50% የመቀነስና የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አጠቀላይ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስ/ቁጥር 0942410695፣ 0913379464 እና 0923072706 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ
✨ messages.ai_summary
Oromia Police College seeks suppliers for beef cattle for trainee meals, vehicle spare parts, water, lighting and electronics items for vehicle servicing. Eligible bidders need a renewed business license, tax registration, VAT registration, and supplier list registration.
