Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address አዳማ ከተማ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 022-211-14-42
  • Website
  • Deadline12 Oct 2026, 10:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00 (አምስትመቶ ብር)
  • Bid Security100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር)
  • opening dateበዛዉ ቀን በ4፡30
  • Categories Vehicles Rent

የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ በከተማው ውስጥ ለሚገኙ አትክልቶች ውሃ የሚያጠጡ 23 ቦቴ መኪናዎች አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በከተማው ውስጥ ለሚገኙ አትክልቶች ውሃ የሚያጠጣ ቦቴ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት /ለመከራየት /ይፈልጋል፡፡

  1. ለተጠየቀው ቦቴ መኪና ኪራይ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax payer registration No) ያላቸው
  2. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጽ/ቤቱ ስም የሲንቄ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1054551161121 ላይ ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት በጽ/ቤቱ የግዢ የስራ ሂደት ቢሮ ድረስ በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመከፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ማንኛውም ተጫራች በሚወዳደርበት ሰነድ ላይ በተሰጠው ስፔሲፊኬሽን መሰረት ብቻ ሳይጨምር ወይም ሳይቀንስ ዋጋውን መሙላት ይኖርበታል፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የተጠቀሰዉን ማስረጃዎች ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  6. ጨረታው የሚከፈተዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛዉ ቀን የስራ ቀን ከሆነ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛዉ ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም በአዳማ ከተማ ገንዘብ/ፅ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ግዢ ክፍል ዉስጥ ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም መ/ቤቱ ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  7. ማንኛውም ተወዳዳሪ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ካሸነፈ ማቅረብ የሚጠበቅበት ሃያ ሶስት /23/ ቦቴዎችን ነው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደርበት እያንዳንዱ ቦቴ አስር ሺህ /10000/ ሊትር እና ከዚያ በላይ የሚይዝ መሆን አለበት፡፡
  10. ተጫራች ለሚያቀርባቸው ቦቴዎች ቦሎ ያስደረገበትን ማቅረብ አለበት፡፡
  11. ተጫራቾች የነዳጅ ዋጋ እና የተለያዩ ጥገናዎችን፣ የሹፌር ወጪን በራሱ ወጪ የሚሸፍን መሆን አለበት፡፡
  12. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከመደበኛ የሥራ ቀናት ውጪ ወይም የበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  13. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺ ህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  14. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0912-22-58-06 ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Adama City Finance Office seeks to rent out 23 water tanker trucks to irrigate vegetables within the city via open bid. Bidders need a valid trade license, updated tax payments, VAT registration, and a taxpayer ID. Each tanker must hold 10,000 liters or more.
Save Tender