Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኅብረት ሥራ ኮሚሽን
  • Address , Phone: 0111263693
  • Website
  • Deadline07 Oct 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00 (አምስትመቶ ብር)
  • Bid Securityሎት አንድ 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር)፤ ሎት ሁለት 10,000.00 (አስር ሺ ብር)
  • opening dateበዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Categories Furniture , Rent , Business Work And Exhibition Work

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኅብረት ሥራ ኮሚሽን አአህስኮ/ብግጨ/አግ/002/2019 ለ2019 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ የኤግዚብሽንና ባዛር እቃዎች (ድንኳን፣ ዲጄና የሙዚቃ ባንድ ከነሙሉ ሳውንድ ሲስተም) ኪራይ አገልግሎት እና የፈርኒቸር ዕቃዎች አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኅብረት ሥራ ኮሚሽን


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አአህስኮ/ብግጨ/አግ/002/2019

የኤግዚብሽንና ባዛር አገልግሎት ግዥና የፈርኒቸር ዕቃዎች ግዥ ግልፅ ጨረታ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህብረት ስራ ኮሚሽን ለ2019 በጀት ዓመት ኤክዚቪሽንና ባዛር ፕሮግራሞች ደረጃውን የጠበቀ የድንኳን፣ የዲጄ እና የሙዚቃ ባንድ ከነሙሉ ሳውንድ ሲስተም እና ሌሎችንም እቃዎች በኪራይ አገልግሎት ግዥ ለአንድ ዓመት የአገልግሎት ግዥውን አወዳድሮ መጠቀም ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ከታች የተዘረዘሩትን የአገልግሎት ግዥ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

ተ.ቁ የሚገዛው እቃ (አገልግሎት) አይነት የሎት ምድብ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን
1 ለኤክዚቭሽንና ባዛር ፕሮግራም እቃዎች ኪራይ አገልግሎት ግዥ ሎት አንድ 50,000
2 የፈርኒቸር እቃዎች ግዥ ሎት ሁለት 10,000

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡-

በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት (VAT15%)፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር ለመከፈሉ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በአንድ ፖስታ ጨረታ እንዲወዳደሩ እየጋበዘ የተጫራቾች መወዳደሪያ መስፈርትና ሁኔታዎችን እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-

  1. በጨረታው የሚወዳደሩት አገልግሎት አቅራቢዎች ለኤክዚቭሽንና ባዛር ፕሮግራሞችን ለማዘጋጀት በታቀደው መሰረት የሚዘጋጅላቸው ቦታ ድረስ ሄደው አገልግሎቱን በራሳቸው ወጭ ገጥመውና ሰርተው ማዘጋጀት አለባቸው፡፡
  2. ኮሚሽኑ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር የአገልግሎቱን ውል ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ እስከ ፕሮግራሙ መጨረሻ አንድ ዓመት ድረስ የሚቆይ ይሆናል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከኮሚሽኑ 3ኛ ፎቅ የግዥ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ማግኘት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለጸው የብር መጠን መሰረት በሲፒኦ ወይንም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ዋስትና (Addis Ababa City Administration Cooperative commission) በማለት በማሸግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ በኮሚሽኑ 3ኛ ፎቅ የግዥ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት ሕዝባዊ ወይም ኃይማኖታዊ በዓል ከሆነ ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ ሌላ ማስታወቂያ ማውጣት ሳያስፈልግ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ይከፈታል፤
  6. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 በተለምዶ መስከረም ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው ቴሌ ጋራጅ አካባቢ ከሚገኘው ካሮጋ ፋርማ ህንፃ

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-126-36-93

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኅብረት ሥራ ኮሚሽን

✨ messages.ai_summary
Addis Ababa City Administration Cooperative Commission seeks bidders for exhibition and bazaar equipment rental (tents, DJ and music band with full sound system) and furniture purchase. Bidders must hold a renewed business license, VAT registration, TIN, and tax clearance.
Save Tender