የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ የቴክኒክና ሙያ መማሪያ መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብስ እና የመኪና እና የሞተር ጎማዎች ግዢ - የገደብ ሀሳሳ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
በምዕራብ አርሲ ዞን በገደብ ሀሳሳ ወረዳ መስተዳድር የገደብ ሀሳሳ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ አርሲ ዞን በገደብ ሀሳሳ ወረዳ መስተዳድር የገደብ ሀሳሳ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- የጽህፈት መሳሪያዎች እና የጽዳት ዕቃዎች
- የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች
- የቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ የመማሪያ መሳሪዎች
- የሰራተኞች የደንብ ልብስ
- የመኪና እና የሞተር ጎማዎች
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው፡፡
- ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ዕቃ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለውና ዕቃዎቹን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ ንግድ ፈቃድ እንዲሁም የ2019 ዓ.ም የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱና TIN No እንዲሁም የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ተካፋይ ለመሆን የምትፈልጉት በምን ዓይነት ዕቃ ላይ እንደሆነ በሰነዶቻችሁ ላይ በትክክል ለይተው መጻፍ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የዕቃ ስም (Brand Name) እና የተመረተበትን ሀገር መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደርበትን የዕቃ አይነት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ በነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር የነጠላ ዋጋ ይወሰዳል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 19/01/2019-09/02/2019 ዓ.ም ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 250.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከገደብ ሀሳሳ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት መግዛት የምትችሉ መሆኑን ይገልጻል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ከነኝት መሆኑና አለመሆኑን በግልጽ በመጥቀስና የድርጅታችሁን ማህተምና ሙሉ አድራሻችሁን በመግለጽ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ዘወትር በስራ ሰዓት በቢሮ ቁጥር 3 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ የሚሆን ለእያንዳንዱ ሰነድ 5000 ብር በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም በጥሬ ብር በገደብ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የሚቀርቡት ዕቃዎች ጥራት ያላቸው እና በስፔስፊኬሽን መሰረት ተሟልተው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ገደብ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ16ኛው ቀን ማለትም 10/02/2019 ዓ.ም የስራ ቀን ጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት 4፡00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤታችን ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00ሰአት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች የአሸነፉትን እቃዎች አጠቃላይ ዋጋውን 10% ቢድ ቦንድ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች VAT ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የደንብ ልብስ ሲቀርብ የምታቀርቡትን አይነት ናሙና መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0912253576/0913819389 መደወል ይችላሉ፡፡
በምዕራብ አርሲ ዞን በገደብ ሀሳሳ ወረዳ መስተዳድር የገደብ ሀሳሳ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Procurement of stationery, cleaning supplies, electronics and office materials, technical and vocational training equipment, staff uniforms, and vehicle and motor tires. Bidders must hold a valid trade license, TIN, and VAT registration, specify brand and origin, and submit uniform samples.
