Tender Detail

Tender Details

  • Company አርሲ ዞን አርባጉጉ የገበሬዎች ሕ/ሥ/ዩኒየን ሀላፊነቱ የተወሰነ
  • Address አርባጉጉ የገ/ሕ/ሥራ/ ዩኒየን አርሲ ዞን መርቲ ወረዳ አቦምሳ : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 21 09 68 80
  • Website
  • Deadline09 Oct 2026, 10:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 1000 (ለእያንዳንዱ፣ የማይመለስ)
  • Bid Securityለእያንዳንዱ ንብረት 10% CPO
  • opening dateበዚሁ እለት በ5:00 ሰዓት (11:00 AM)፣ አዳማ ከተማ መብራት ሀይል ተስፋዬ አሎፒክ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
  • Categories Cargo Vehicle , Disposal Sale , Agricultural Materials , Machinery And Vehicles

ያገለገለ ኤፌሰር (FSR) የጭነት መኪና እና ሁለት ትሬሸሮች ሽያጭ - አርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን (ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ)

አርሲ ዞን አርባጉጉ የገበሬዎች ሕ/ሥ/ዩኒየን ሀላፊነቱ የተወሰነ


ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

አርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃ/የተወሰነ ያገለገለ አንድ ኤፌሰር የጭነት መኪና የጃፓን ስሪት የሆነ ሞዴሉ 2014 እና ሁለት ትሬሸሮች በትራክተር ተጎትቶ የተለያዩ ሰብሎችን የሚወቁ የቱርክ ስሪት የሆኑ ሱፐር ቱርቧቸው 1200 የሆኑ ትሬሸሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::

በዚሁ መሰረት:-

በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን::

  1. ለጨረታው የወጣ ንብረትነቱ ኤፌሰር (FSR) የጭነት መኪና የጃፓን ስሪት ሞዴል 2014 ንብረትነቱ የአርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን የሆነ ተሽከርካሪ የሰሌዳ ቁጥር አአ-05-0243 የሊብሬ ቁጥር 401648 የሻንሲ ቁጥር JALK6A139E7102061 የሞተር ቁጥር 6HH1-473615 ሙሉ ሰፖንዳ ያለው ፤ (መነሻ ዋጋ 6,500,000 (ስድስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር )እንደሆነ እንገልፃለን ::
  2. ሁለት ትሬሸሮች በትራክተር ተጎትቶ የተለያዩ ሰብሎችን የሚወቁ የቱርክ ስሪት የሆኑ ሱፐር ቱርቧቸው 1200 የሆኑት የአንዱ መነሻ ዋጋ 650,000 (ስድስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ) ሲሆን የሁለቱ ዋጋ አንድ ላይ 1,300,000 (አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺህ ብር ) መሆኑን እንገልፃለን።
  3. ተጫራቾች የማይመለስ ለእያንዳንዱ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በአርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን አዳማ መጋዘን ሙገር አካባቢ ታደሰ አበበ ህንፃ ጀርባ ካለው ጊቢ ውስጥ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ::
  4. ተጫራች ግለሰብ ወይም የገበሬ አባል ከሆነ የዘመኑ የናሽናል ID (ዲጂታል መታወቂያ) እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር ያለው መሆኑን የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ፤ ድርጅት ከሆነ የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር መክፈሉን የሚገልጽ መረጃ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ አለበት። እንዲሁም ሌሎች ተቋማት/ማህበራት ከሆኑ የተመዘገቡበትን ህጋዊ ሰርተፍኬት የውክልና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾቹ የግል ድርጅት ወይም የመንግስት ድርጅት ከሆነ የውክልና ደብዳቤ እና የናሽናል ID (ዲጂታል መታወቂያ) ማቅረብ አለበት ::
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለያንዳንዱ ለጨረታው ለቀረቡት ንብረቶች 10% CPO በማቅረብ መጫረት ይችላሉ::
  7. ለጨረታው ለቀረቡት ንብረቶች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 10:00 (ሰዓት) ድረስ በአርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን አዳማ መጋዘን ሙገር አካባቢ ታደሰ አበበ ህንፃ ጀርባ ካለው ግቢ ውስጥ ኤፌሰር የጭነት መኪናውን ማየት ይችላሉ ::
  8. ለጨረታው የቀረቡትን ሁለት ትሬሸሮች በአርሲ ዞን በጮሌ ወረዳ በአርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን መጋዘን ያለበት ግቢ ውስጥ በግልፅ ማየት ይችላሉ::
  9. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ንብረት ዓይነት የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ በመሙላት ቴክኒካል ዶክመንትና ፋይናንሽል ዶክመንት አንድ(1) ኦርጅናል እና አንድ(1) ኮፒ በተለያዩ ፖስታ አዘጋጅተው አንድ ላይ በማሸግ ሌሎች የተጠየቁትን መስፈርቶች በመጨመር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  10. ጨረታው በ11ኛ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ጀምሮ ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዳማ ከተማ መብራት ሀይል ተስፋዬ አሎፒክ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ተዘግቶ በ5:00 ሰዓት ላይ በዚሁ ቦታ ይከፈታል::
  11. ጨረታው 11 ኛ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከረፋዱ 4:30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዳማ ከተማ መብራት ሀይል ተስፋዬ አሎፒክ ህንፃ 2ኛ ፎቅ በዚሁ እለት በ5:00 ሰዓት ላይ በዚሁ ቦታ ይከፈታል::
  12. ተጫራቹ ጨረታውን ካሸነፉበት ቀን ጀምሮ በሁለተኛ ቀን የግዢና ሽያጭ ውል ተፈራርሞ በ10 ቀን ውስጥ ሙሉ ክፍያ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈውን ንብረት መውሰድ አለበት::
  13. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  14. የጨረታው አሸናፊ ከሽያጭ በኋላ ከስም ማዛወሪያ ጋር ተያይዞ ያሉትን ወጪዎች ከፍሎ ስሙን ወደ ራሱ ያዛውራል ::

ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ አድራሻው ከላይ በተገለፀው በዩኒየኑ መጋዘን በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0921096880/0920063165/0916894185 ደውለው መረዳት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን::

አድራሻችን:- አርሲ ዞን መርቲ ወረዳ አቦምሳ ከተማ 01ቀበሌ መሆናችንን እንገልፃለን::

አርሲ ዞን አርባጉጉ የገበሬዎች ኅ/ሥ/ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ::

አርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃ/የተወሰነ

✨ messages.ai_summary
Arbagugu Farmers' Cooperative Union is selling by open bid a used Japanese FSR cargo truck (Model 2014) and two Turkish-made tractor-drawn trailers (super turbo 1200) for harvesting crops. Bidders must submit a technical and financial document, one original and one copy, in separate envelopes.
Save Tender