Tender Detail

Tender Details

  • Company Oromia Agricultural Cooperatives Federation (የኦሮሚያ የግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ)
  • Address ጀሞ ሚካኤል አደባባይ ሚካኤል ቤ/ክ ጎን OACF ህንፃ 6ኛ ፎቅ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 12 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ , Phone: 0910645442
  • Websitehttps://www.oromiacooperativefederation.org/
  • Deadline19 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500
  • Bid Securityየዋጋውን 5% (CPO, የ90 ቀን ዋስትና ያለው)
  • opening dateበዚሁ ዕለት በ4:30 (ከጠዋቱ 10:30 AM)
  • Categories Car Decoration Materials , Tire And Spare Parts , Vehicle Spare Parts

የተለያዩ የመኪና ጎማዎች ግዥ - የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ

Oromia Agricultural Cooperatives Federation (የኦሮሚያ የግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ)


የጨረታ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ የተለያዩ የመኪና ጎማዎችን ግዥ በሰነድ ላይ ባለው መስፈረት መሰረት በዘርፉ ላይ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማሟላት የጨረታ ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን፡፡

  1. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታ ሰነዱን ከኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 ተከታታይ ቀናት ብቻ መውሰድ ይቻላል፡፡
  2. ተጫራቾች በዚህ የንግድ ዘርፍ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ ቲን፣ ቫት፣ የንግድ ምዝገባ እና ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የ90 ቀን ዋስትና ያለው ቢድ ቦንድ ሲፒኦ ከጨረታ መክፈቻ ቀን ጀምሮ የሚቆጠር የዋጋውን 5% (አምስት ፐርሰንት) በታሸገ ፖስታ (ኤንቨሎፕ)የድርጅቱን ማህተም በመምታት ከዶክመንት ጋር ለብቻው ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  4. ጨረታው የሚገባበት እና የሚከፈትበት
    • ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ (ኤንቨሎፕ) በማሸግ የድርጅቱን ማህተም በመምታት በ22ኛው ቀን እስከ ከ4:00 ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
    • ጨረታው በዚሁ እለት 4:00 የሚዘጋ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት በ4:30 ይከፈታል፡፡
    • የጨረታ መክፈቻው ቀን የዕረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  5. የመወዳደሪያ መስፈርቶችን ሙሉ ለሙሉ ላሟሉ ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ታይቶ አሸናፊው ተጫራች ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ይሆናል፡፡
  • ከላይ የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች በሙሉ አሟልተው የማያቀርቡ ተጫራቾች ከጨረታው የሚሰረዙ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ጀሞ ሚካኤል አደባባይ ሚካኤል ቤ/ክ ጎን OACF ህንፃ 6ኛ ፎቅ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 12

ስልክ፡- 0910645442

የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን

✨ messages.ai_summary
The Oromia Agricultural Cooperatives Federation invites eligible suppliers to bid for the supply of various vehicle tires. Bidders must hold a valid trade license, TIN, VAT, and business registration. The lowest-priced compliant bid wins. Incomplete submissions will be disqualified.
Save Tender