የሳኒተሪ እቃዎች፣ የአልሙኒየም በርና መስኮት፣ PVD Coated golden mirror፣ ስካይ ላይት እና አልሙኒየም ሲሊንግ አቅርቦት እና ገጠማ ስራ - ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን (ጨረታ ቁጥር 03/2019-06/2019)
ZEMEN CONSTRUCTION CORPORATION (ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን)
ጨረታ ቁጥር
03/2019፣04/2019፣05/2019 እና 06/2019
ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እየገነባቸው ላሉት
- ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የሳኒተሪ እቃዎች አቅርቦት እና አቅርቦትና ገጠማ ጨረታ ቁጥር 03/2019
- ለክለላ ከተማ አስተዳደር ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የአልሙኒየም በርና መስኮት እና PVD Coated golden mirror አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ጨረታ ቁጥር 04/2019
- ለወግዲ ወረዳ አስተዳደር አዳራሽ ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ ስካይ ላይት፣ አልሙኒየም ሲሊንግ እና የአልሙኒየም በርና መስኮት አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ጨረታ ቁጥር 05/2019
- ለደባርቅ ንግድና ገበያ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የአልሙኒየም በርና መስኮት አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ጨረታ ቁጥር 06/2019 ግዥ ለመፈጸም ህጋዊና ብቃት ያላቸው ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማዛት ይፈልጋል። ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤
- በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው/ያላት፤
- የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፤
- የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 እና አ/አበባ ለገሃር አመልድ ህንፃ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ 7ኛ ፎቅ ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለጨረታ ቁጥር 03/2019፣04/2019፣05/2019 እና 06/2019 እስከ 15ኛው ቀን (15 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር) ባህር ዳር ዋናው ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሣጥኑ ለጨረታ ቁጥር 03/2019፣ 04/2019፣ 05/2019 እና 06/2019 በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ታሽጎ 8:30 ይከፈታል። የተጠቀሱት የመክፈቻ እና የመዝጊያ ቀናቶች የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8:00 ሠዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በእለቱ ቀን 8:00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8:30 ይከፈታል።
- የጨረታው ውድድሩ በሎት/በምድብ/ ድምር ዋጋ የሚታይ ሲሆን በአንድ ሎት ምድብ ለተጠቀሱ የስራ ዝርዝሮች ሙሉ በሙሉ ዋጋ መሞላት አለበት።
- በጨረታ የተሞላው ዋጋ የጨረታ ሠነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ45 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆያል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር
ባህርዳር -058-218-0538 /09-18-01-06-17/09-18-16-43-93/09-12-00-21-87/09-21-25-8920/09-21-26-13-00
አዲስ አበባ :- ስልክ ቁጥር 0111265338/09-18-80-03-64 /09-11-90-86-29
የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
✨ messages.ai_summary
Zemen Construction Corporation seeks eligible factories and suppliers for the supply and installation of sanitary ware, aluminium doors and windows, PVD coated golden mirrors, skylights, and aluminium ceilings across various projects. Bidders must hold a valid trade license, TIN, and VAT registration certificate.
