Tender Detail

Tender Details


የአዳማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለሥልጠና እና ለቢሮ የሚውሉ የICT፣ እስቴሽነሪ፣ የኤሌክትሪክ፣ ፈርኒቸር፣ የኮንስትራክሽን፣ የአውቶሞቲቭ፣ የሆቴል፣ የልብስ ስፌት፣ የውበት፣ የጫማና ቆዳ ማሠልጠኛ እና የጽዳት መሣሪያዎች ግዥ

Adama Polytechnic College (የአዳማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)


የጨረታ ማስታወቂያ

የአ/ፖ/ቴ ኮሌጅ በ2019 ዓ.ም በጀት ለሥልጠና ለቢሮ ውስጥ የሚውል የICT እና እስቴሽነሪ መሳሪያዎች የኤሌክትሪክ፣ ፈርኒቸሮች፣ የኮንስትራክሽን ዕቃዎችን፣ የአውቶሞቲቭ፣ ለሆቴል ማሰልጠኛ፣ ለልብስ ስፌት (Garment &Textile)፣ ለውበት ማሰልጠና እቃዎች፣ ለጫማና ቆዳ ማሠልጠኛዎችን በጽዳት መሣሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ

  1. በየሥራ መስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ወይም ለመክፈላቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡
  3. የአቅራቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00/ሃምሳ ሺህ በባንክ በተመሰከረ ቼክ (CPO)ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 400.oo/አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ በመሙላት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ኮሌጅ ለዚህ ጨረታ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ በ2 ፖስታ አድርጋችው ማስገባት አለባቸው፡፡
    ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከቀኑ በ8:00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዛው ዕለት በ9:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫት ያካተተ መሆን አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ የቀረበው ዋጋ ቫት ያካተተ እንደሆነ ተቆጥሮ ይወሰዳል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ በጨረታው ያሸነፈባቸው ዕቃዎች እስከ በጀት አመቱ መጨረሻ ሲ.ታዘዝ ኮሌጅ ድረስ በራሱ ወጭ ማቅረብና የዕቃው ጥራት በተጠቃሚው ሲረጋገጥ ብቻ ርክክብ የሚደረግና ክፍያ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
  9. ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ለተጨማሪ መረጃ ስ.ቁ 0221115245 ወይም 0902322891 /0912249692 ማነጋገር ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡- አዳማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አዳማ ከተማ ደደቻ አራራ ወረዳ

በኦሮሚያ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ቢሮ
የአዳማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

✨ messages.ai_summary
Adama Polytechnic College seeks suppliers for ICT, stationery, electrical, furniture, construction, automotive, hotel, garment, beauty, shoe & leather training, and cleaning equipment. Bidders need a renewed trade license, TIN, tax payment proof, VAT registration, and supplier evidence.
Save Tender