የሠራተኛ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ፣ የህክምና፣ የትምህርት እና የጽዳት ዕቃዎች፣ ህትመት፣ ፕላንትና ማሽነሪ ጥገና፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች እና ቋሚ ዕቃዎች ግዥ - የሐምሌ 1 ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት
ሐምሌ ፩ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት
የመጀመሪያ ዙር ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የሐምሌ1 ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ለ2019ዓ.ም የተለያዩ ለት/ት ሥራ የሚውሉ የሠራተኛ የደንብ ልብስ፣አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ህትመት፣ አላቂ የህክምና ዕቃዎች፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣ አላቂ የጽዳት እቃዎች፣ ፕላንትና ማሽነሪ ጥገናዎች ልዩ ልዩ መሳሪያዎች እና ቋሚ ዕቃዎች ተጫራቾችን አወዳድሮ በጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች፡-
- በአቅራቢነት የተመዘገቡ፣
- በተጠቀሰዉ የስራ ዘርፍ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸዉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸዉንና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸዉ፣
- ተጫራቾች በየሎቱ በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪ በCPO በትምህርት ቤቱ ስም በተጠቀሰው ሎት ለደንብ ልብስ፡-6500፣ ለአላቂ የቢሮ ዕቃዎች፡ 5000፣ የህትመት ስራዎች፡- 2000 አላቂ የህክምና ዕቃዎች፡- 7000፣ ለአላቂ የትምህርት ዕቃዎች፡-7500፣ ለአላቂ የፅዳት ዕቃዎች፡-6500፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፡-6000፣ ለፕላንት እና ለማሽነሪ ጥገና፡- 2500፣ ቋሚ ዕቃ መግዣ፡-7000 የጨረታ ማስከበሪ ማስያዝ ግዴታ አለባቸው፡፡
- የአሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ በተገለፀበት ከሰባት/7/ ቀን ጀምሮ ውል መፈፀምና 10%/አስር ፐርሰንት/ የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 04 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጉ ዕቃዎች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ሰነዱ ላይ የተጠቀሱትን ዕቃዎች የሚሸጡበትን ዋጋ እና ሌሎች መረጃዎች በታሸገ እንቨሎፕ ለዚህ በተዘጋጀ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
- ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት /በ11ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 04 ይከፈታል ከስራ ቀን ዉጭ ከሆነ ግን በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነዉ፡፡
አድራሻ፡- ወሎ ሰፈር ዳንዲ ቦሮ ት/ቤት አጠገብ
ስልክ ቁጥር፡- 0115-57-44-63 / 011-5-15-25-69
የሐምሌ 1 ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት
✨ messages.ai_summary
The school seeks suppliers for staff uniforms, consumable office, medical, educational and cleaning supplies, printing, plant and machinery maintenance, various equipment and fixed assets. Bidders must be registered suppliers with a valid license, tax and VAT registration, and submit samples where required.
