Tender Detail

Tender Details

  • Company በሸካ ዞን የማሻ ወረዳ ፋይናንስ ኢ/ል/ጽ/ቤት
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline12 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 300 (ሦስት መቶ) ብር የማይመለስ
  • Bid Securityብር 5000 (አምስት ሺህ) ብር በባንክ የተረጋገጠ C.P.O
  • opening dateበዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
  • Categories Cleaning & Janitorial , Office Supplies And Services

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በሸካ ዞን በማሻ ወረዳ ፋይናንስ ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለማሻ ወረዳ ሴ/ር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡

በሸካ ዞን የማሻ ወረዳ ፋይናንስ ኢ/ል/ጽ/ቤት


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በሸካ ዞን በማሻ ወረዳ ፋይናንስ ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለማሻ ወረዳ ሴ/ር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡

ሎት 1ኛ የተለያዩ የጽ/መሣሪያ ዕቃዎች

ሎት 2ኛ የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች

ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ከላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል

በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን ማሟላት የሚችሉትን ተጫራቾች ይጋብዛል፡፡

  1. በመስኩ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለውና የ2019 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችልና ተጨማሪ የእሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዳቸዉ ብር 5000 (አምስት ሺህ) ብር በባንክ የተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ) ብር ከማሻ ወረዳ ገ/ባ/ሥ/ቅ/ጽ/ቤት በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ከማሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 (ሁለት) መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት ማሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለዚህ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ ።
  5. ጨረታው በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት (አራት) ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በ16ኛው ቀን የመንግሥት ሥራ ሰዓት ካልሆነ በሚቀጥለው በመንግስት የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል
  6. የጨረታው አሸናፊ የሆነው አቅራቢ ዕቃዎቹን አጓጉዞ በሸካ ዞን በማሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ማቅረብ አለበት፡፡
  7. ተጫራች የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ለማስያዝ ፍቃደኛ መሆን አለበት ።
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 0475580293 ወይም 0912789043 ወይም 0917868185 ደውለው

በሸካ ዞን የማሻ ወረዳ ፋይናንስ ኢ/ል/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Masha Woreda Finance Office seeks suppliers for various office equipment (Lot 1) and cleaning materials (Lot 2) for woreda offices. Bidders need a valid business license, supplier registration, and VAT registration. The winner must deliver goods to Masha Woreda Finance Office.
Save Tender