የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ለመስሪያ ቤቱ የመኪና ዕቃ (Spair part) ከህጋዊ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Oromia Land Bureau (የኦሮሚያ መሬት ቢሮ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ለመስሪያ ቤቱ የመኪና ዕቃ (Spair part) ከህጋዊ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ድርጅቶች የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ከስቶክ ያለውና ውል ገብቶ በተባለው ጊዜ ውስጥ የመኪና ዕቃ (Spar part) ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ በመከፈል በኦሮሚያ መሬት ቢሮ 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ለመወዳደር ዋጋ 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የዕቃዎቹን የዋጋ ዝርዝር በጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማስፈርና ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶክመንት ኦርጅናልና ኮፒውን የፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒውን ቴክኒከል ዶከመንትና CPO በተለያየ በአምስት (5) በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም ከቀኑ በ7፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ ወይም ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
የጨረታው አሸናፊ አካል በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ዕቃውን ጨርሶ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በዚህ ስልክ ቁጥር መጠቀም ይችላሉ።
0910622700/0919519951/0946653304/094944572/
አድራሻ፡- ሳርቤት አደባባይን ዞሮ ወደ ቄራ መሄጃ ዋናው አስፋልት 200 ሜትር ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስሪያ ቤቶች ቅጥር ግቢ ውስጥ
የኦሮሚያ መሬት ቢሮ
✨ messages.ai_summary
The Oromia Land Bureau seeks to purchase vehicle spare parts from eligible suppliers. Bidders must be registered for VAT, have a TIN, be on the suppliers list, and be able to deliver from stock within the agreed time. Partial or full cancellation of the tender is reserved.
