Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን
  • Address አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ፒያሳ/እስታቲክስ እናት ህንጻ ፊት ለፊት ዋስትና ንግድ ማአከል 15ኛ ፎቅ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-27-68-25
  • Website
  • Deadline05 Oct 2026, 9:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300 ብር (ሶስት መቶ ብር ብቻ) (non-refundable)
  • Bid Security20,000 ብር (ሃያ ሺ ብር ብቻ) CPO
  • opening dateበ11ኛው ቀን ከጠዋቱ3፡30
  • Categories Vehicles Rent

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን


ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2019

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

በ2019 በጀት ዓመት የመኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. ሎት 1 የፒክ አፕ መኪና፣ የሚዲባስ መኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡- ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ
  2. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. ከገቢዎች የተወዳዳሪነት ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፣
  5. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /Tin No/ ያላቸው፤
  6. በመንግስት ግዥና የንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ድረ-ገጽ (WWW.PPA.gov.et)
  7. ተጫራቶች የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ/CPO/
    • ሀ. የፒክ አፕ መኪና በኤሌክትሪክ--20,000 ብር (ሃያ ሺ ብር ብቻ) CPO
    • ለ. የሚዲባስ መኪና---20,000 ብር (ሃያ ሺህ ብር ብር) CPO
    • ሐ. የፒክ አፕ መኪና በነዳጅ -20,000 ብር (ሃያ ሺህ ብር ብቻ) CPO
  8. ተጫራቶች በባንክ የተረጋገጠ በመ/ቤታችን ስም CPO ማስያዝ አለባችሁ ነገር ግን CPO ያላስያዘ ቢኖር ከጨረታ ውጪ ይሆናል፣
  9. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመወዳደር ጨረታው ከተዘጋጀ በኋላ የሚወዳደሩበት በተሰጠው በእስፔስፍኬሽን መሰረት መቅረብ አለበት፤
  10. ማንኛውም ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 7 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ 15ኛ ፎቅ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በመቅረብና የማይመለስ 300 ብር /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፣
  11. አሸናፊው ድርጅት ጥራቱን ያልጠበቀ ዕቃ ወይም አገልግሎት ካቀረበ በራሱ ወጪ የመለወጥ ግዴታ አለበት፡፡
  12. መ/ቤቱ ካቀረበው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ በአማራጭነት ማቅረብ አይቻልም፤
  13. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል ኦርጅናልና እና ኮፒ ከዛ ደግሞ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ ዋጋ ሞልታችሁ በተናጠል ለየብቻ በፖስታ አድርጋችሁ የድርጅታችሁን ማህተምና ፊርማ የተወዳደራችሁበትን የሎት አይነት በፖስታው ላይ እየጻፋችሁ አስገቡ ካልጻፋችሁበት ደግሞ ፖስታችሁ እንደማይከፈት እያወቃችሁ የተባሉትን በሙሉ በማድረግ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ወደ ህንጻው ስትግቡ በቀኝ በኩል ባለው ሊፍት 15ኛ ፎቅ ፊት ለፊት ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፡፡
  14. ጥቃቅንና እንስተኛ ተጫራቾች ለምትጫረቱባቸው ዕቃዎች (አገልግሎቶች) የጨረታ ሰነዱን በነፃ ለመውሰድ
    • ሀ. ካደራጃችሁ መ/ቤት ደብዳቤ ማምጣት አለባችሁ፣
    • ለ. ሰነዱን በነፃ ለመውሰድ በመመሪያ መሰረት ለምታቀርቡት ዕቃ (አገልግሎቶች) አምራች መሆን አለባችሁ፤
  15. ተጫራቶች መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በትክክል መሙላት አለባቸው፡፡
  16. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈበት ዕቃ ወይም አገልግሎት ላይ ውል ሲገባ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፣ እንዲሁም አሸናፊ የሆነው ድርጅት እሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ጨረታ ተከፍቶ ውጤት ከተለጠፈ ከ8 የሥራ ቀናት በኋላ በመ/ቤታችን ቀርቦ ውል መግባት አለበት፡፡
  17. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ጋዜጣው ከወጣበት ከ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ 3፡30 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ከኛ ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የሥራ ቀናት ውስጥ የሚከፈት ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  1. ተጫራቾች የቀረበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑንና ያላካተተ መሆኑን መግለጽ አለባችሁ ይህ ካለሆነ ግን መ/ቤቱ ያቀረበውን ዋጋ ቫትን እንዳካተተ አድርጎ ይወስደዋል፡፡
  2. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ክፍስ ከተማ ስሪዳ ወረዳ፣ 1 ፒያሳ አስታቲክስ ጎን እናት ህንጻ ፊት ሰፌ ዋስትና ንገድ ማእከል 15ኛ ፎቅ ላይ ይገኛል፡፡

መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-127-68-25 ይደውሱ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን

✨ messages.ai_summary
Addis Ababa City Administration Light Service Authority seeks vehicle rental services via Lot 1: pickup, minibus, and electric/fuel pickup vehicles. Bidders must have a valid business license, VAT registration, tax ID, and a revenue competitiveness letter.
Save Tender