የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አፋር ሪጅን የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
Afar Region Electric Service
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EEU/CER/S/C&PSG-002/2019
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አፋር ሪጅን የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን ግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
| ተ.ቁ | ተፈላጊው የእታው ዝርዝር | መለኪያ | የጨረታ ማስከበሪያ | ጨረታው የሚከፈትበት ቀን |
| 1 | Desk Top Computer | በቁጥር | 250,000 | መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 |
| 2 | Printer | በቁጥር | ||
| 3 | Lap top | በቁጥር | ||
| 4 | air conditioner | በቁጥር | ||
| 5 | Refrigerator | በቁጥር |
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማሩ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ ያለው ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የታክስ ከፋይነት ቲን /Tin/ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ዌብሳይት ላይ የተመዘገቡ መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት በአፋር ሪጅን ሰፕላይ ቼን ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 100015078235 በመከፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደርያ ሰነዳቸውንና የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ሲፒኦ /cpo/ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ አፋር ሪጅን ሳፕላይ ቼን ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ለዚሁ ስራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በተመሳሳይ ቀን መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት በኢትዮጲያ ሰዓት አቆጣጠር ይከፈታል፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር 033-366-83-36 መደወል ይችላሉ።
- ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የአፋር ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት
✨ messages.ai_summary
Afar Region Electric Service seeks to buy various electronics via open tender: desktop computers, printers, laptops, air conditioners, and refrigerators. Eligible bidders must have a valid business license, Ministry of Finance registration certificate, and TIN. Bidders must also be registered on the Procurement Agency website.
