Tender Detail

Tender Details


የአገና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ/መ/ክልል በጉራጌ ዞን ከወልቂጤ ከተማ 42 ኪሜ ከቡታጅራ 38 ኪሎ ሜትር ርቀትና ከአዲስ አበባ 196 ኪ ሜትር ላይ በአገና ከተማ የሚገኝ ኮሌጅ ሲሆን በ2019 ዓ.ም በጀት አመት የሚያስፈልጉን የሥልጠና ግብዓቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የአገና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር አ/ፖ/ቴ/ኮ/001/2019

የአገና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ/መ/ክልል በጉራጌ ዞን ከወልቂጤ ከተማ 42 ኪሜ ከቡታጅራ 38 ኪሎ ሜትር ርቀትና ከአዲስ አበባ 196 ኪ ሜትር ላይ በአገና ከተማ የሚገኝ ኮሌጅ ሲሆን በ2019 ዓ.ም በጀት አመት የሚያስፈልጉን የሥልጠና ግብዓቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ አቅራቢዎች ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት የስልጠና ክፍሎች ለማቅረብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. Hardware and Network Servicing (ICT)
  2. Industrial Electrical Machine Derives Technology
  3. Automotive Technology
  4. Hotel and Tourism Management
  5. General Metal Fabrication and Assembling Manufacturing (Mechanics)
  6. Building Electrical Installation
  7. Furniture Making
  8. Masonery (Onsite Constraction MGT)
  9. Structural Constraction work
  10. Basic Electrical Equipment Service.
  11. Office Stationery and Vehicles Materials
  12. Textile /Garment Technology

በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን የስልጠና ዕቃዎች ለማቅረብ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፡-

  1. በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው አቅራቢዎች ማስረጃቸውን ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑ ግብር የከፈሉ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  2. ተጫራቶች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ የስራ ቀናት በማይመለስ ብር(500) አምስት መቶ ብር ብቻ) በኮሌጁ አካውንት ቁጥር 1000168288248 በማስገባት ስሊፕ ይዘው መምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታው ሰነድ በኮሌጁ ግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 16 ለተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 6፡00 ድረስ መግዛት ይጠብቅባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የዘመኑ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ የስራ ቀናት በ21 ቀን 6፡00 ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች የእቃውን ዋጋ የእቃውን አይነት በጨረታ ሰነዱ በተጠቀሰው መሰረት ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታው ሙሉ ሰነድ ሞልተው ኦርጂናል እና ፎቶ ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦድ 1.5% በባንክ የተመሰከረለት (CPO) በኮሌጁ አቅራቢያ በሚገኙ በንብ ኢንተናሽናል ባንክ፤ ብርሀን ባንክ፤ አቢሲኒያ ባንክ፤ በአዋሽ ኢንተናሽናል ባንክ፤ በዘምዘም ባንክ እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ በአገና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስም በማሰራት ኦርጅናል ዶክመንት በማያያዝ በፖስታ ውስጥ ማቅረብ ይጠበቅባቸል፡፡
  7. ተጫራቾች ሌላው ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  8. ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. የጨረታ አሸናፊዎች ዋናውን እቃ ከማስገባታቸው በፊት ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. ጨረታውን ያሸነፈው አካል ህጉን በሚፈቅደው መሰረት 3% (Withholding) የመክፈል ግዴታ አለባቸው፡፡
  11. የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉት እቃ ወደ ኮሌጁ ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0113290387 / 0113290569 4- 0113290168
* Email: agenapoly.college/@gmail.com

በጉራጌ ዞን የአገና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

✨ messages.ai_summary
Agena Poly Technic College seeks suppliers for training materials across ICT, electrical, automotive, tourism, metal fabrication, construction, furniture, textile and office supplies. Eligible bidders need a renewed trade license, tax compliance, VAT registration, and supplier registration. Samples required before main supply delivery.
Save Tender