Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline16 Oct 2026, 9:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ (non-refundable)
  • Bid Securityብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee)
  • opening dateጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ቀኑ 9፡30 ሰዓት
  • Categories Maintenance And Repair , Installation, Maintenance And Other Engineering Services

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ (ዋና መስሪያ ቤት) የሚገኙ የሽያጭ ማሽኖች የጥገና እና የማሻሻያ (ማዘመን) በድጋሜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ (ReBid for Vending Machine Repair and Upgrade) ሥራዎችን ለማቅረብ ፈቃደኛ ለሆኑ ብቁ የአገልግሎት አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


በድጋሜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: -SSNT-T643

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ (ዋና መስረያ ቤት) የሚገኙ የሽያጭ ማሽኖች የጥገና እና የማሻሻያ (ማዘመን) በድጋሜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ (ReBid for Vending Machine Repair and Upgrade) ሥራዎችን ለማቅረብ ፈቃደኛ ለሆኑ ብቁ የአገልግሎት አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-

1.      በሽያጭ ማሸኖች የጥገና ፤ የማሻሻያ (ማዘመን) እና ተዛማጅ አገልግሎቶች ህጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ፤ የግብር ከፋይ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ፍቃድ ያላቸው ማንኛውም ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

2.    ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T643 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ የጨረታ ቁጥሩን፣ የድርጅታቸውን ስምና ስልክ ቁጥር ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።

3.    ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) “በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ” ስም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል።

4.    ተጫራቾች በጨረታው  ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል ሰኞ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ቀኑ 9፡ዐዐ ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ:

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል

አሸብር ተሾመ በስልክ ቁጥር፡ +251-115-17-49-18 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

ኢሜል: ashebirte@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Airlines Group seeks qualified service providers to repair and upgrade vending machines at Bole International Airport (Head Office). Bidders must hold a valid business license for vending machine repair, upgrade and related services, a tax payer certificate, VAT registration, TIN, and eligibility for government tenders.
Save Tender