Tender Detail

Tender Details

  • Company የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ /ኢ/ል/ጽ/ቤት
  • Address ሚዛን አማን ከተማ : ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline07 Oct 2026, 9:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceበነጻ
  • Bid Securityለሎት አንድ 20,000/ሃያ ሺህ ብር/ ለሎት ሁለት 5,000/አምስት ሺህ ብር/ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ቼክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክሬዲት
  • opening dateለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሠዓት
  • Categories Furniture And Furnishing , Printing And Publishing

የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለሚ በሚ/አ/ከ/አስ/ር ስር ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገ/ት የሚውሉ

የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ /ኢ/ል/ጽ/ቤት


ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለሚ በሚ/አ/ከ/አስ/ር ስር ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገ/ት የሚውሉ

ሎት 1፡- ፈርኒቸር ዕቃዎች

ሎት 2፡- የህትመት ስራዎች በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላል።

1.      ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2.      የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።

3.      በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ኦንላይን የተመዘገቡና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

4.      የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።

5.      ግብር ስለመክፈላቸው ከገቢዎች መ/ቤት ክሊራንስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

6.      የጨረታ ሰነድ ከግዥ ኬዝ ቲም የሥራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን /በነጻ በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ።

7.      የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ሲመልሱ ህጋዊነት ሰነድ እና ፋይናንሻል የተሞላበትን ሰነድ 1 ኦርጅናልና 1 ኮፒ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8.      የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ 20,000/ሃያ ሺህ ብር/ ለሎት ሁለት 5,000/አምስት ሺህ ብር/ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ቼክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክሬዲት ለሚ አ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በማለት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

9.      ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ4፡00 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።

10. ሰነዱን ሞልተው ወደ ጨረታ ሳጥን ለማስገባት ሲመጡ ተመዝግበውና ፈርመው ማስገባት አለባቸው።

11. በጨረታ ማስታወቂያ ላይ የቃላት ወይም የትርጉም ስህተት ቢኖር በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጠው የበለጠ ተቀባይነት ይኖረዋል።

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Mizan Aman City Administration Finance Office seeks bidders for furniture (Lot 1) and printing works (Lot 2) for its offices. Bidders must have a renewed business license, VAT registration, online supplier registration, TIN, and tax clearance.
Save Tender