Tender Detail

Tender Details

  • Company በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ፅ/ቤት የቀበና ጤና ጣቢያ
  • Address ቀበና ሼል የኦሮሚያ ደን ህንፃ ገባ ብሎ ቀበና መድሀኒዓለም ቤተክርስቲያን አጠገብ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-124 4294
  • Website
  • Deadline01 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 200 /ሁለት መቶ ብር/
  • Bid Security8,000.00 /ስምንት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/
  • opening dateበዚሁ ዕለት 4፡30
  • Categories Cleaning & Janitorial , Health Care, Medical Industry , Office Supplies And Services

በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የቀበና ጤና ጣቢያ የፋይናንስና ግዥ በጨረታ ቁጥር ቀ/ጤ/ጣቢያ 1/2019 በጀት ዓመት ለጤና ጣቢያው አቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ፅ/ቤት የቀበና ጤና ጣቢያ


የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ግዥ መለያ ቁጥር የቀ/ጤ/ጣ/01/2019 ዓ.ም

በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የቀበና ጤና ጣቢያ የፋይናንስና ግዥ በጨረታ ቁጥር ቀ/ጤ/ጣቢያ 1/2019 በጀት ዓመት ለጤና ጣቢያው አቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  • ሎት 1 አላቂ የቢሮ የጽሕፈት መሣሪያዎች
  • ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች
  • ሎት 3 የደንብ ልብስ እና ስፌት
  • ሎት 4 የተለያዬ የጥገና እቃዎች
  • ሎት 5 ቋሚ እቃዎች እና ኮምፒውተር ተዛማች እቃዎች
  • ሎት 6 ህትመት
  • ሎት 7 ኮምፒውተር ተዛማች እቃዎች ጥገና
  • ሎት 8 ፍሳሽ ቆሻሻ ማንሳት የኮምፒውተርና ተዛማች ዕቃዎች ጥገና
  • ሎት 9 መድኃኒቶች፣ የላብራቶሪ ሪኤጀንት፣ አላቂ የሕከምና ዕቃዎች ቋሚ የሕከምና ዕቃ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት-

  1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው ቫት ተመዝጋቢ የሆነ የዘመኑን ግብር የከፈለበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡና የአቅራቢነት ዝርዝርውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና ቲን ነምበር ያላቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቀበና ጤና ጣቢያ ፋይናንስ ክፍል ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት እቃ 8,000.00 /ስምንት ሺህ ብር/ በባንክበተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራቾች ሰነዱን ለማስገባት በሚመጡበት ጊዜ ሳምፐል ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ሳምፕል አብሮ ማስገባት አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን ከሲፒኦ ጋር በአንድ ፖስታ ኮፒ ሰነድ በሌላ ፖስታ አሽገው የድርጅቱን ማህተም በማድረግና በፊርማ በማረጋገጥ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-6፡00 ሰዓት እንዲሁም 7፡30-11፡00 ሰዓት ድረስ የጤና ጣቢያው የግ/ን/አስ/ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታው ሳጥን በ11ኛ የሥራ ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች/ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአራዳ ከ/ከተማ በቀበና ጤና ጣቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የአንዱ ዋጋም ሆነ ጠቅላላ ዋጋ ሲቀመጥ ቫት አካቶ መሆን አለበት፡፡
  7. ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራቾች በተመዘገቡበት ንግድ ፍቃድ ዘርፍ ብቻ መወዳደር አለባቸው፡፡
  8. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ ውል ከተፈራረመበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀን ውስጥ እስከ ጤና ጣቢያው ንብረት ከፍል በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  9. የጨረታ ሰነድ የዝዙበትን ኦርጅናልና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ከገዙት የጨረታ ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡ ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- አድራሻ ቀበና ሼል የኦሮሚያ ደን ሕንፃ ገባ ብሎ ቀበና መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን አጠገብ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር፡- 011-8-11 21 55 / 0111 23 56 07 ደው ሰው መጠየቅ ይችላሉ

በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የቀበና ጤና ጣቢያ

✨ messages.ai_summary
Qebena Health Station seeks suppliers for office stationery, cleaning materials, uniforms, maintenance items, fixed assets, computers, printing, computer repair, waste removal, medicines, lab reagents, and medical equipment. Bidders need a valid trade license, VAT registration, tax compliance, and MoFED supplier registration.
Save Tender