አዲሲቷ ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/መ/የገንዘብ የቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር ዘመናዊ የኮር ባንኪንግ ሲስተም (CBS) ለማቅረብ፣ ለመጫን፣ ለማበጀት (Customization)፣ ስልጠና ለመስጠት እና የጥገና አገልግሎት ለማቅረብ ብቁና ተፈላጊውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች የታሸጉ የጨረታ ሰነዶችን እንዲያቀርቡ ይጋብዛል።
አዲሲቷ ኢትዮጵያ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ ስራ ማህበር
የጨረታ ጥር ማስታወቂያ
ድርጅት፡ አዲሲቷ ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/መ/የገንዘብ የቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር
የፕሮጀክት ስም፡ የኮር ባንኪንግ ሲስተም (Core Banking Solution) ግዥና ትግበራ
የማጣቀሻ ቁጥር፡ AECBS 001
የወጣበት ቀን፡ መስከረም 04 ቀን 2019 ዓ.ም. / Sep 14, 2026
አጠቃላይ መግለጫ
አዲሲቷ ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/መ/የገንዘብ የቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር ዘመናዊ የኮር ባንኪንግ ሲስተም (CBS) ለማቅረብ፣ ለመጫን፣ ለማበጀት (Customization)፣ ስልጠና ለመስጠት እና የጥገና አገልግሎት ለማቅረብ ብቁና ተፈላጊውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች የታሸጉ የጨረታ ሰነዶችን እንዲያቀርቡ ይጋብዛል።
የሥራ ወሰን
ተመራጩ አቅራቢ የሚያቀርበው ጠንካራ የሶፍትዌር ሲስተም የሚከተሉትን የሥራ ክፍሎች ማካተት አለበት፦
- የአባላት ምዝገባ እና የአክሲዮን የአባልነት አስተዳደር
- የቁጠባና ተቀማጭ ሂሳብ አስተዳደር
- የብድር ማመልከቻ፣ ሂደት፣ ክትትል እና ግምገማ
- የጠቅላላ ሂሳብ መዝገብ (General ledger) እና የፋይናንስ ሪፖርት
- የመተሳሰሪያ ቻናሎች (ሞባይል ባንኪንግ፣ AIM ወይም USSD)
- የሲስተም ደህንነት፣ በሚና ላይ የተመሠረተ የመጠቀሚያ ፈቃድ እና የመረጃ ማስተላለፍ (Data Migration)
የተሳትፎ መስፈርቶች
ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የሚከተሉትን ህጋዊና ቴክኒካዊ ሰነዶች ማቅረብ አለባቸው፦
- ትክክለኛና ተቀባይነት ያለው የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት
- የግብር ክሊራንስ ማስረጃ
- በፋይናንስ ተቋማት በተለይ በቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበራት (SACCOs) የኮር ባንኪንግ ሲስተም በመተግበር የተረጋገጠ ልምድ ያለው
- ከሶፍትዌሩ ዋና አምራች (OEM) የተሰጠ የተፈቀደ ወኪልነት ወይም የአጋርነት ሰርተፊኬት (እንደ አግባብነቱ)
የጨረታ ዝርዝር ሁኔታ
- የጨረታ ሰነድ መግዣ/መውሰጃ፡ ሙሉ የጨረታ ሰነዱን ከቢሮአችን ሾላ ገበያ፣ ለምለሚ መርካቶ ህንፃ፣ 4ኛ ፎቅ ማግኘት ይቻላል።
- የጨረታ ሰነድ ዋጋ፡ 1,000 (አንድ ሺህ) ብር፣ በCBE ሂሳብ ቁጥር 1000218597975 በአዲሲቷ ኢትዮጵያ የቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር ስም የሚከፈል።
- የጨረታ ማቅረቢያ የመጨረሻ ቀን፡ Sep 30, 2026 ከቀኑ 9፡00 ሰዓት (03:00 PM)። ዘግይተው የሚቀርቡ ጨረታዎች ተቀባይነት አያገኙም፡፡
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
የመገኛ መረጃ
አድራሻ፡
ሾላ ገበያ፣ ለምለሚ መርካቶ ህንፃ፣ 4ኛ ፎቅ
የካ ክፍለ ከተማ
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0994 40 40 61/51 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አዲሲቷ ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/መሰ/የቁ/ብ/የህ/ስራ ማህበር
✨ messages.ai_summary
Addis Ethiopia SACCO invites bids to supply, install, customize, train on, and maintain a modern Core Banking System. Scope covers member and share management, savings/deposits, loans, general ledger and reporting, mobile/USSD channels, security, role-based access, and data migration. Bidders must meet licensing, tax, SACCO CBS experience, and OEM authorization requirements.
Not stated in the notice: bid security. Check the original document or ask the issuer.
