Tender Detail

Tender Details


የኦሮሚያ ስቪል ምዝገባ ኤጀንሲ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ውስጥ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በ2019 በጀት አመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የኦሮሚያ ሲቪል ምዝገባ ኤጀንሲ


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ/የግዥ መለያ ቁጥር OCRA/NCB/01/2019

የኦሮሚያ ስቪል ምዝገባ ኤጀንሲ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ውስጥ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በ2019 በጀት አመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታዉ ለመሳተፍ

  1. በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረገጽ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ወይም ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ቢሮ የተሰጣቸው የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት፤ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. በሚወዳደሩበት ዘርፍ የተሰማሩበትን የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
  4. በእንግሊዘኛ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000.00 /one thousand birr/ በመከፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ከኤጀንሲው ፋይናንስ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጥቅል /የሎት/ ዝርዝር ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነድ ውስጥ የተቀመጡ የብር መጠን በባንክ ክፍያ ማዘዣ የተረጋገጠ /CPO/ ወይም ቅድመ ሁኔታ ያላስቀመጠ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች ለሁሉም የግዥ ዓይነት ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻ በፓስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው
  7. ተጫራቾች መወዳደሪያ ሰነዳቸውን በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በኤጀንሲው ግዢ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከ1/1/2019 ቀን ጀምሮ እስከ 25/1/2019 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው 25/1/2019 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዝያው እለት ከቀኑ 5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኦሮሚያ ስቪል ምዝገባ ኤጀንሲ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
  9. ኤጀንሲው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ አድራሻ የኦሮሚያ ሲቪል ምዝገባ ኤጀንሲ ሳር ቤት ከጨፌ ኦሮሚያ ጽ/ቤት ጎን ስልክ ቁጥር 0913263370/0920416224

Lot No. Item No. Description Unit of Measurement Quantity
1 1.1 Biometric Tablet PCS 800

የኦሮሚያ ስቪል ምዝገባ ኤጀንሲ

✨ messages.ai_summary
Oromia Civil Registration Agency seeks to procure 800 biometric tablets through open tender. Bidders must be registered suppliers or hold a valid registration certificate, VAT and taxpayer certificates, and a renewed business license. Technical and financial documents must be submitted separately in sealed envelopes.
Not stated in the notice: bid security. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender