Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address በጉራጌ ዞን ከወልቂጤ ከተማ 42 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ 197 ኪ.ሜ ላይ : ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0113290317
  • Website
  • Deadline06 Oct 2026, 2:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Bid Security20,000(ሀያ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠለት ሲ'ፒአ (ጥሬ ገንዘብ)
  • opening dateበዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30
  • Categories Health Care, Medical Industry , Pharmaceutical Products

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው ግብርና ልማት ጽ/ቤት የእንስሳት መድሀኒቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው ግብርና ልማት ጽ/ቤት የእንስሳት መድሀኒቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች መስፈርቱን የምታሟሉ

1.ሎት1 የእንስሳት መድሀኒት

  1. በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላችሁና የዘመኑ ግብር በመከፈል ፍቃድ ያደሳችሁ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. በመድሀኒት አቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ከጠቅላላ ገንዘብ 20,000(ሀያ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠለት ሲ'ፒአ (ጥሬ ገንዘብ) በእዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን መድሀኒቶች እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መጋዘን ድረስ አጠቃላይ በአንድ ጊዜ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታው ዝርዝር የያዘ ዶከመንት ለመግዛት የሚያስችል የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ሰነዳቸው ፋይናንስ ጽ/ቤት ግ/ን/አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
  7. ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀ ቀን ጀምሮ በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% /በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች በጨረታው ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ውል ማስከበርያ አሰርቶ ውል ካልፈፀሙ መስርያ ቤቱ የጨረታ ማስከበርያውን የመውረስ መብት አለው፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታው ሰነዳቸው አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማለትም ቅዳሜና እሁድ እዲሁም የበዓል ቀናት ጨምሮ አየር ላይ ይውላል:: ጨረታው በ16ኛ ቀን ከቀኑ 8፡00 ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  10. ጨረታው በ16 ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገርግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት ጨረታው ከመከፈት እያስተጓጉለውም፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ተጫራቾች የተጫረቱባቸው መድሀኒቶች ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው፡፡
  13. መድሀኒቶቹ ሁሉንም እስከ ፋይናንስ ማስረከብ ድረስ ያለው ወጪ ከተወዳዳሪው ይሆናል፡፡
  14. እየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡

ማሳሰቢያ፦ ወረዳው በጉራጌ ዞን ከወልቂጤ ከተማ 42 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ 197 ኪ.ሜ ላይ ነው::

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁ. 09-23-51-95-14/09-13-37-12-45/09-11-07-70-93

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

/አገና/

✨ messages.ai_summary
The Finance Office of Enjja Woreda in Gurage Zone, Central Ethiopia Regional State, seeks to purchase veterinary medicines through open tender for the Woreda Agriculture Development Office. Bidders must hold a valid license, tax clearance, TIN, and pharmaceutical supply registration, and deliver all medicines at once to the office warehouse.
Save Tender