Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ
  • Address ቃሊቲ ቆርኪ ፋብሪካ ፊት ለፊት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 4552358
  • Website
  • Deadline02 Oct 2026, 10:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) የማይመለስ
  • Bid Securityብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና
  • opening dateበዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Categories Spare Parts , Car Decoration Materials , Tire And Spare Parts , Vehicle Spare Parts

በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ አመት ውል በመዋዋል (በማዕቀፍ ስምምነት) ለመግዛት ይፈልጋል።

በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ


የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥው መለያ ቁጥር፡- ት/ልአ/ዘ ግዥ ብ/ግ/ጨ/01/2019

በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ ከዚህ በታች ለተጠቀሱት የተለያዩ መለዋወጫዎች፦ (Iveco, Tracker Isuzu, Nisan and Eitcher, Toyota, Hyundai, Dongfong Daewoo bus, Sunlong bus, ZNA rich pickup, Kia Automobile, Lifan Automoble and Addis Geely Automobile የመኪና ዕቃ መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር የግዥ መስፈርቶቹን የሚያሟሉ እና በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ አመት ውል በመዋዋል (በማዕቀፍ ስምምነት) ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት በጨረታው ላይ ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ለ2018 2019 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ወይም ጨረታው እስከ ሚከፈትበት ቀን ድረስ ሊያገለግል የሚችል የንግድ ስራ ፈቃድ፡ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ ክሊራንስ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን እነዚህ ሰነዶች በኦርጅናልና ኮፒ በመለየት በማሸግና በመግለጽ ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ከላይ የተገለጹትን ሰነዶች ከጨረታ ሰነድ ማቅረቢያው ቀነ ገደብ በፊት ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለሚወዳደሩበት የመኪና ዕቃ መለዋወጫ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል ከመስከረም 11/2019 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ሰዓት እንዲሁም ከሰአት ከ7፡30-1፡30 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ሰዓት ድረስ ግዥ ክፍል አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 17 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ። (አድራሻው ከስር ተገልጿል።)
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ መስከረም 22 ቀን 2019 ከጠዋቱ 4፡30 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  5. ተጫራቶች ከላይ ለተጠቀሰው የመኪና ዕቃ መለዋወጫ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ዘርፍ ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው። ኢንሹራንስ ቦንድና ቼክ ተቀባይነት የላቸውም። ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲው ለብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።
  6. ተጫራቾች የቴከኒከ መወዳደሪያ የቴከኒከ ሰነድ እና የፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻ በፖስታ በማሸግና ኮፒ እና ኦሪጅናል የፋይናንሻል እንዲሁም የቴከኒካል ሰነድ ኮፒዎችን ለየብቻ በፖስታ በማሸግ በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ሁሉንም ፖስታዎች በማድረግ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። እድራሻ ከታች ተገልጿል።
  7. አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ መጠን 10 ፐርሰንት /አስር ፐርሰንት/ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ ስም እሰርተው ውሉን የሚፈጽሙ ይሆናል፡፡ እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱ እቃው በመነጋጋር ለአንድ አመት የሚቆይ ውል በመዋዋል በውሉ መሰረት የምንረካከብ ይሆናል።
  8. ዘርፉ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ የሀብት አስተዳደርና ግዥ ዋና ክፍል

አድራሻ፦ አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጣሳና ኮርኪ ፋብሪካ ፊት ስፌት ሸገር ህንፃ አከባቢ አስ በጅምላ ጊቢ ውስጥ

ስልክ ቁጥር፡- 011 4552358

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Trading Businesses Corporation's Transport and Logistics Service Sector seeks to procure various vehicle spare parts (Iveco, Isuzu, Nissan, Toyota, Hyundai, Daewoo, Sunlong, Kia, Lifan, Geely and others) via open national tender, awarding a one-year framework agreement contract to legally registered suppliers meeting the stated requirements.
Save Tender