Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline26 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O
  • opening dateጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure

2055ካ/ሜ ሆኖ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ።

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት ኑኑ ተሾመ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ገነት ተሾመ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ/37518 በ6/04/2007 ዓ.ም በኮ/መ/ቁ/115914 በ10/3/2017 ዓ/ም በኢታቂ ቃሊቲ ከ/ተማ ወረዳ 01 የቤ.ቁ 144 የሆነ በእነ ወ/ሮ ዘውዲቱ ተሾመ ባሕረ ስም ተደራጅቶ የሚገኝ የይዞታው ነባር ይዞታ ቢሆንም የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የሌለው (ሰነድ አልባ ይዞታ) አጠቃላይ የይዞታው ስፋት 1988 ዓ.ም የGIS መረጃ መሠረት 2100 ካ/ሜ ሲሆን በአካል የተገኘ በተወሰደ ልኬት መሠረት 2055 ካ/ሜ ሆኖ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 58,339,755 (ሃምሳ ስምንት ሚሊዮን ሦስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ አምስት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ ተይዞ በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡፡ ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.115914 በ12/12/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ድጋሚ ሐራጅ ሆኖ 1/4ኛ 14,584,938.75 (አስራ አራት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰማንያ አራት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ስምንት ከ75/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡ የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ 1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ C.P.O የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሠርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሠርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የፈዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃጸም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
A 2,055 sq.m. unregistered property in Addis Ababa (Kaliti, Woreda 01) is re-auctioned by the Federal Courts Execution Office. Bidders must deposit 1/4 of the estimate via CPO, pay transaction tax, and settle the full amount within 15 days. Inspection allowed on three working days.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender