Tender Detail

Tender Details

  • Company የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address AMHARA Ethiopia, Phone: 0911579138
  • Website
  • Deadline27 Sep 2026, 3:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceየኢትዮጵያ ብር 500 / አምስት መቶ ብር /
  • opening dateጨረታው አየር ላይ ለተከታታይ 15 ቀን ቆይቶ በ 16 ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • Categories Pharmaceutical Products , Vehicle Spare Parts

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለላስታ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል፡- ሎት 01 የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ አቃዎች/ስፔር ፓርት ፤ ሎት 02 የተለያዩ የእንሰሳት መድሃኒቶች በመደበኛ በጀት እና በሪቮልቪንግ ፈንድ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨ/መለያ የቁ/ግንአስ-069/2018

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለላስታ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል፡- ሎት 01 የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ አቃዎች/ስፔር ፓርት ፤ ሎት 02 የተለያዩ የእንሰሳት መድሃኒቶች በመደበኛ በጀት እና በሪቮልቪንግ ፈንድ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡

  1. በአዲሱ የንግድ አዋጅ መሠረት በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ነበር/ የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆናቸዉን የገቢ ኬላ ሊራንሰ እና የቫት ሰርተፍኬት ያላቸውና ለእንሰሳት መድሃኒቱ የሚሞሉት ዋጋ ከ500,000/ከአምስት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 500 / አምስት መቶ ብር / በመክፈል ላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው አቃዎች (ፐርፎርማንስ ቦንድ) በታወቀ ባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሆነ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /Unconditional Bank Guarantee/ ለመኪና እቃዎች በቁርጥ 70,000/ሰባ ሺህ ብር እና ለእንሰሳት መድሃኒቶች በቁርጥ 10,000/ አስር ሺህ ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከፖስታው ውስጥ አብሮ መግባት ወይም ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን ለንሰቶ የሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በ 16ኛው ቀን፡- ሎት 01 የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች/ስፔር ፓርት ሎት 02 የእንሰሳት መድሃኒቶች ጧት 3፡30 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ላይ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  5. የተጠቀሰው ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም በካላንደር ዝግ ከሆነ ለሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይተላለፋና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን ኮፒና ኦርጅናል በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  7. አሸናፊው አካል እቃዎችን በራሱ ትራንስፖርት ላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  8. የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  9. ማንኛውም እቃ ጽ/ቤቱ በሚፈልገውና ባዘጋጀው አስፔሲፊኬሽን መሰረት ስለሚቀርብ በሙከራና በባለሙያ አረጋግጦ የሚረከብ መሆኑ ይታወቅ፡፡
  10. ተጫራቾች በአንድ ሎት ውስጥ የተዘረዘሩትን የእቃ አይነቶች ከፋፍሎ መሙላት አይቻልም ውድድሩ በየሎት ምድቡ ጥቅል ብር ወይም ድምር ስለሆነ የሁሉም ዋጋዎች መሞላት አለበት፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ወይም ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመቅረብ ወይም ከዚህ በታች በተጠቀሱት ስልክ ቁጥሮች 03333601249 ወይም 091579138 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አስተዳደር ዞን የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Supply of various vehicle spare parts (Lot 1) and various veterinary medicines (Lot 2) for Lasta Woreda sector offices, under regular and revolving fund budgets via open bid. Bidders need a renewed business license, TIN, tax clearance, income gate license, and VAT certificate (VAT required if veterinary medicine bid exceeds 500,000 ETB).
Save Tender

Procurement of Spare Parts

READ MORE
Procurement of Spare Parts

READ MORE