በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 1 ግንቦት 20 ጤና ጣቢያ በ2019 በጀት ዓመት የሚከተሉትን እቃዎች እና አገለግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 1 ግንቦት 20 ጤና ጣቢያ በ2019 በጀት ዓመት የሚከተሉትን እቃዎች እና አገለግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ሁሉም ተጫራቾች እንድትሳተፉ አንጋብዛለን፡፡
| ተ.ቁ | የእቃው ዓይነት | የጨረታ ማስከበሪያ በብር |
| 1 | አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች | 5,850 (0.5%) |
| 2 | አላቂ የፅዳት አቃዎች | 6,500 (0.5%) |
| 3 | ቋሚ የቢሮ እቃዎች | 9,500 (0.5%) |
| 4 | የህትመት ውጤቶች | 3,030 (0.5%) |
| 5 | የደንብ ልብስ | 4,505 (0.5%) |
| 6 | የመድኃኒትና የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች | 22,150 (0.5%) |
| 7 | መሠረተ ልማት | 7,605 (0.5%) |
| 8 | ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች አድሳትና ጥገና አገልግሎት | 1,450 (0.5%) |
| 9 | የመኪና ኪራይ | 1,050 (0.5%) |
ተጫራቾች
- በዘርፉ ከተሰማሩበት ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ተገቢዎች ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በድህረ ገፅ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው በኦላይን የሚረጋገጥ ይሆናል።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ቲን ነበር ማቅረብ የሚችሉ።
- የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ 200 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነድ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 409 ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።
- ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 401 ድረስ በመምጣት ሙሉ የጨረታ ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- አነስተኛ እና ጥቃቅን በሚያመርቱት ምርት ብቻ ከክፍያ ነፃ ሰነድ ይወስዳሉ። እንዲሁም ካሸነፉ በኋላ የውል ማስከበሪያ ማስከበሪያ ከተደራጁበት ወረዳ ደብዳቤ ማምጣት አለባቸው።
- ጨረታው በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾቹ ሲያሸንፉ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና የሚቀርብባቸውን አቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን አቃ በራሱ ትራንስፖርት ወጪ የመሥሪያ ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ገቢ ማድረግ አለበት።
- ጤና ጣቢያው በጨረታ ሰነድ ውስጥ ላይ ከተጠቀሰው 20% ድረስ የመጨመር እና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው ጸንቶ የሚቆየው ሰ60 ቀን ነው።
- ተጫራቾቹ የጨረታውን ማስከበሪያ ሲፒኦ በየሎቱ ARF ማሠራት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ሲፒኦ ኮፒ እና ኦርጅናል ይዞ መምጣት አለባቸው።
- ተጫራቾች መደበኛ የጨረታ ሰነዱ ላይ በየአንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ማህተብ እና ፊርማ ካላደረጉ ከውድድር ውጪ ይሆናሉ፡፡
- ተወካዮች ውል ለመዋዋልና ለተለያየ አገልግሎት ሲመጡ የውክልና ደብዳቤ ይዘው መምጣት አለባቸው።
- ጤና ጣቢያው ተጫራቾች ውል ተዋውለው ለሚያቀርቡት እቃ ላይ እስከ 6 ወር ድረስ በተመሳሳይ ዋጋ 20 በመቶ ተጨማሪ ግዥ ማከናወን ይችላል።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- አ/ከ/ከ/ከተማ ወረዳ 1 ግንቦት 20 ጤና ጣቢያ ልዩ ቦታው መርካቶ አሜሪካን ግቢ ኡራጎ ሕንፃ ጀርባ የመን ኮሚኒቲ ት/ቤት አጠገብ
ስልክ ቁጥር፡- 0112732872/0822732594/012732584
አዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ የወረዳ 1 ግንቦት 20 ጤና ጣቢያ
✨ messages.ai_summary
Addis Ketema District 1 Ginbot 20 Health Station seeks suppliers for consumable stationery, cleaning supplies, durable office items, printed materials, uniforms, medical equipment, infrastructure, electronics repair, and vehicle rental. Eligible bidders need a valid trade license, tax compliance, VAT and TIN certificates, and supplier registration.
