Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Sugar Industry Group (የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ)
  • Address ሜክሲኮ አካባቢ ከሚገኘው አልሳም ጨለለቅ ህንፃ ፊት ለፊት፣ ፌሊፒስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: +251115500417
  • Websitehttps://etsugar.com/esig/
  • Deadline24 Sep 2026, 2:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 500.00 (ብር አምስት መቶ)
  • opening dateበዚሁ ቀን 8፡15
  • Categories Agriculture And Farming , Raw Materials

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለ2019 ዓ.ም የምርት ዘመን ለስኳር ምርት ግብዓትነት የሚያገለግል ትኩስ ኖራ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር (LP/OT/02/SIG/2018/19)

  1. የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለ2019 ዓ.ም የምርት ዘመን ለስኳር ምርት ግብዓትነት የሚያገለግል ትኩስ ኖራ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
  2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ ለ2018/19 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስከር ወረቀት/ የታከስ ከሊራንስ ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No.) ሠርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ የሚመለከተው የመንግስት አካል ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች አገልግሎት ሰጪ ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን/መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡
  3. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 1000000888862 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መከፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ፣ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6:00፣ ከሰዓት በኋላ ከ7:00-11:00 ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  1. የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
  2. ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ
  3. አድራሻ አዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ
  4. ጨስስቅ አልሳም ህንጻ ፊት ስፊት
  5. ፊሲፔስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220
  6. ስልክ ቁጥር +251 11 5516271 115-500417
  7. አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
  1. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 3 በተገለፀው አድራሻ መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡15 ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተመሠከረለት የከፍያ ማዘዣ (CPO) ከቴከኒክ መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለስልሳ (60) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
  4. የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለሰላሳ (30) ቀናት ይሆናል፡፡
  5. ግሩፑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Sugar Industry Group seeks eligible firms to supply fresh lime for sugar production. Bidders must provide a renewed trade license, tax clearance, TIN, VAT registration, and supplier registration certificate.
Save Tender