የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ለግንባታ መስሪያ እና ለፈርኒቸር የሚሆን ጥራት ያለው ጥለይ ውድ ጣውላ አምራች ድርጅት ነው፡፡
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ለግንባታ መስሪያ እና ለፈርኒቸር የሚሆን ጥራት ያለው ጥለይ ውድ ጣውላ አምራች ድርጅት ነው፡፡ ስለሆነም ፋብሪካው ለዚህ ምርት ግብዓት የሚሆን 180 ቶን ግሉ ፓውደር/ Urea formaldehyde powder resin glue/ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት
- በትከክለኛው የስራ መስክ የተሰማራና የንግድ ስራ ፈቃዱን ያሳደሰ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው
- የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታው ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፤
- ተጫራቾች ለግሉ ፓውደር ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ 700,000.00 (ሰባት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትእዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፤ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፤ ካለም እንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፤
- ማንኛውም ተጫራች ኦሪጅናል የጨረታ ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ለተከታታይ 16 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ በአዲስዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን/ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ ውስጥ በይፋ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ከመከፈት አይታገድም፡፡
- የመከፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም በህዝብ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፤
- አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ከተጠቀሰው ብዛት ወይም መጠን በታች ቀንሶ መጫረት አይቻልም፡፡
- አቅራቢ ድርጅቱ የማስጫኛ እና የማስወረጃ እንዲሁም ሌሎች ወጪዎችን ሸፍኖ ንብረቱን ለካምፓኒው ንብረት ክፍል ያስረከባል፡፡
- ካምፓኒው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011637 58 03 ደውለው ይጠይቁ
የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር ደ/ብርሃን
✨ messages.ai_summary
Debere Berhan Wood Processing invites bids for 180 tons of urea formaldehyde powder resin glue, used as raw material for construction and furniture panel production. Open to licensed, VAT-registered suppliers with a valid TIN. Bidders must submit copies of relevant documents. The supplier covers loading, unloading, and delivery costs.
