Tender Detail

Tender Details

  • Company የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
  • Address ጎንደር ከተማ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0581-26-03-06
  • Website
  • Deadline29 Sep 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 300/ሶስት መቶ/
  • opening dateSep 29, 2026 2:30 PM
  • Categories Spare Parts , Petroleum Products Fuel, Diesel , Oil And Lubricant , Vehicle tire

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ አገልግሎት ለሚሰጣቸው ተቋማት ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል፡-


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ አገልግሎት ለሚሰጣቸው ተቋማት ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል፡-

  1. ሎት 1 የተለያየ መኪና መለዋወጫ እቃ
  2. ሎት 2 የመኪና ጎማ እና ባትሪ
  3. ሎት 3 የመኪና ነዳጅ፣ ዘይትና ቅባት በግልጽ ጨረታ በማወዳደር አመታዊ ውል ይዞ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

ማቅረብ የምትችሉት መረጃ፡-

  1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ
  2. የግብር መለያ ቁጥር TIN ያላቸው
  3. የገንዘብ መጠኑ ከ500,000 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርበታል።
  4. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. የሚገዛው እቃ ዝርዝር መግለጫ/specification ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል።
  6. ለእያንዳንዱ ሎት ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ/ቢድ ቦንድ/ ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ/ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ/ በመክፈል ጎን/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 15 መውሰድ ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሃሳባቸውን አንድ ወጥ በሆኑ ዋናና ቅጅ በማለት የመጫረቻ ሰነድ በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ጎን/ከ/አስ/ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ስዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. ተጫራቾች ዋጋውን በሚሞሉበት ወቅት ስርዝ ድልዝ ካደረጉ ከውድድር ውጭ ያስደርጋል።
  10. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ሙሉ ስምና ፊርማቸውን እንዲሁም የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
  11. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት በጎንደር ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 11 በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ። ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ ጥሪአችንን አክብረው ባይገኙም ጨረታው በሌሉበት ይከፈታል። የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  12. ማንኛውም ተጫራች የሚቀርብ ቅሬታ ካለ ጨረታው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከ5 የስራ ቀናት በኋላ የሚቀርብ ቅሬታ የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን።
  13. ለእቃው የተሞላው ዋጋ የፋይናንስ ግምገማ ሲደረግ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት /አርቲሜቲክ ቼክ ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት ወደላይም ሆነ ወደታች እስከ 3% ድረስ ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ የበለጠ ወይም ያነሰ ልዩነት ካጋጠመ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
  14. ተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ ጎን ከተ/አስ/ ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር፡- 058 126 0306 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

P.o.box-192 Tele-058 126-0306
Fax-058 111-7563
email- gontipco@ethionet.et

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ አገልግሎት

✨ messages.ai_summary
Supply of vehicle spare parts, tires, batteries, fuel, oil and lubricants for institutions served by Gondar City Administration Finance Directorate, under an annual contract. Bidders need a valid trade license, TIN, and VAT registration if the amount exceeds 500,000 birr. Specifications are attached to the tender document.
Save Tender