Tender Detail

Tender Details

  • Company በደቡብ ወሎ ዞን የሐይቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን
  • Address , Phone: 033-222-0162
  • Website
  • Deadline30 Sep 2026, 10:54 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) የማይመለስ
  • opening dateበ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Categories Building Construction , Construction Works

በአ.ብ.ክ.መ. ደቡብ ወሎ አስተዳደር ዞን የሐይቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2019 በጀት ዓመት በUNDP በጀት በቀበሌ 2 አስተዳደር ክልል ሎት 1.


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአ.ብ.ክ.መ. ደቡብ ወሎ አስተዳደር ዞን የሐይቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2019 በጀት ዓመት በUNDP በጀት በቀበሌ 2 አስተዳደር ክልል ሎት 1. ትምህርት ቤት መማሪያ ክፍል ግንባታ ስራ፤ሎት 2 የቀበሌ 2 ቢሮ አስተዳደር ግንባታ ስራ በግልፅ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት፤-

  1. በዘመኑ የታደሠ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፤
  2. የብቃት ማረጋገጫ ምሥክር ወረቀት ያላቸው ፤
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  4. የኤክሳይዝ ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፤
  5. የበጀት አመቱ ተገቢውን የታክስ እና ግብር ግደታ የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ የታክስ ክሊራስ ማቅረብ የሚችል
  6. የዕቃ ወይም የአገልግሎት ግዥው መጠን ብር 200,000.00 ( ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 ( አምስት መቶ ብር ) በመክፈል ሐይቅ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፣ ፋይ/ንብ/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት 1 ትምህርት ቤት መማሪያ ክፍል ግንባታ ስራ ብር 52,500፣ ሎት 2 የቀበሌ 2 ቢሮ አስተዳደር ግንባታ ስራ ብር 47,500፤ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቢድ ቦንድ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  9. የጨረታ ሰነዱን ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ ሐይቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፣ ፋይ/ንብ/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 20 ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  10. ጨረታው በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጐ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ( ባይገኙም ይከፈታል )ቅዳሜና ዕሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይፈፀማል።
  11. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል የማይችል ሲሆን፤ በጨረታ ሠነዱ የሠጠውን ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም።
  12. የሂሳብ ስሌት ( አርቲሜቲክ ቴክ ) በዥ ፈፃሚው መ/ቤት ባለሙያ ከሚስተካከለው ውጭ በተጫራቾች የሚቀርበው የመጫረቻ ሠነድ ላይ በነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውጭ ይሆናል።
  13. ተጫራቾች ለሥራው የሚያስፈልጉ ማሽነሪዎችንና የሠው ኃይልን በሙሉ ራሣቸው ችለው ነው።
  14. ተጫራቾች ከደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርባቸዋል።
  15. ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው
  16. የህንፃ ሥራ ተቋራጭ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፤
  17. አሸናፊው የሚለየው በሎት ጠቅላላ ዋጋ ሲሆን፤ በቴክኒካልና ፋይናንሽያል ድምር ውጤት ነው።
  18. በቴክኒካልና ፋይናንሽያል የሚቀርቡ መረጃዎች ግልፅና ጎላ ብለው የሚነበቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
  19. ጽ/ቤቱ እንደ በጀቱ ሁኔታ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ሥራዎች ብዛት 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል።
  20. የትምህርት ቤት መማሪያ ክፍል ግንባታ ስራ፤ እና የቀበሌ 2 ቢሮ አስተዳደር ግንባታ ሥራዎች ጥራታቸው የተጠበቀ መሆን አለበት።
  21. አሸናፊው ድርጅት ሥራውን ጥራቱን ጠብቆ እንዳጠናቀቀ ገንዘቡን ወጪ አድርጐ ይወስዳል።
  22. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  23. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033-222-0162 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።

በደቡብ ወሎ ዞን የሐይቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን

✨ messages.ai_summary
Construction of a school classroom (Lot 1) and Kebele 2 administrative office (Lot 2) in Hayik Town, South Wollo Zone, under the UNDP budget. Bidders must hold a valid business license, Grade 5 or above, VAT and excise tax registration, tax clearance, and cover all machinery and labor.
Save Tender