Tender Detail

Tender Details


የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ የቤት እቃ ኮንስትራክሽን፣ አልባሳት፣ አስፔርፓርት፣ የፅዳት አቃትራ ምግብ ነክ እና ልዩ ልዩ በሐራጅ እና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ የቤት እቃ ኮንስትራክሽን፣ አልባሳት፣ አስፔርፓርት፣ የፅዳት አቃትራ ምግብ ነክ እና ልዩ ልዩ በሐራጅ እና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን እቃዎች 05/01/2019 ጀምሮ ሳምፕል በማየት አና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይነልፅል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤
  2. ለሐራጅ ጨረታው 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት የእቃ አወጋገድ ቢሮ በ“ባይሽ” ሲፒኦ (CPO) ማቅረብ የሚችል፤
  3. በግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ ከረፋዱ 400 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መነሻ ዋጋ እራሱ ያቀርባል፤
  4. በግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
  5. ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የዛውን እቃ ከያዘው በ5 ቀናት ውስጥ የሚከፍል መሆኑ፤
  6. እቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲፒኦ (ር.80) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤
  7. በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤
  8. አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤
  9. ማንኛውም ተጫራች እቃዎቹን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ እንደየቦታው እርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፤
  10. ተጫራቹ እቃዎቹን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቤቱ ሀላፈነቱን አይወስድም፤
  11. ተጫራቾች የሞሉትን የጨረታ ሰነድ ከቀን 05/01/2019 ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ መቅረብ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ07/01/2019 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
  12. የሐራጅ ጨረታው የሚካሄደው አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) አሸናፊ ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፍል መሆኑ፤

በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Jigjiga Customs Office seeks to sell confiscated contraband goods—electronics, home décor, furniture, construction materials, clothing, spare parts, cleaning supplies, and food items—via auction and open bid. Eligible bidders must have a valid trade license, TIN, VAT registration, tax payment proof, and residency ID.
Save Tender